የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች አሉታዊ ተጽእኖ
ረቡዕ፣ መጋቢት 22 2013
ማስታወቂያ
የማኅበራዊ መገናኛ አውታሮች አጠቃቀም በኢትዮጵያ የፖለቲካ ምህዳር ውስጥ የሚያደርሰው ሀገርን የሚጎዳ አሉታዊ ጫና እየጨመረ መምጣቱ ተገለጸ። በመደበኛ መገናኛ ብዙሃን ላይ እምነት ማጣት ብሎም ሀሳብን በነፃነት ማስተናገድ ያለመቻል ችግር ፣ትልቅ የሆነው ይህ ዘርፍ አፍራሽ ተፅዕኖው መጨመሩ ዛሬ በአዲስ አበባ በተደረገ ውይይት ላይ ተነግራል።ማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የፖለቲካ ተሳትፎን በማሳደግ፣ ሰዎችን ለበጎ በማሰባሰብ እና በማነሳሳት የማይናቅ አወንታዊ ሚና ቢኖራቸውም አሉታዊ ተፅእኗቸው እየበለጠ መሆኑ በጥናት ተመላክቷል። ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት እንዳለ ሆኖ ግጭትና ልዩነትን የሚያበረታቱ የዘርፉ አጠቃቀሞች ላይ ሕጋዊ የቁጥጥር ሥርዓት መዘርጋት እንዳለበትም በውይይት ላይ ተጠይቋል።
ሰሎሞን ሙጬ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ