ማስታወቂያ
ኤመራልድ፣ ኦፓል እና ኒኬልን የመሳሰሉ ማዕድናት የቀረቡበት አውደ ርዕይ በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ በመታየት ላይ ይገኛል። ለጌጣጌጥ እና ለኢንዱስትሪ ግብዓት የሚውሉ በርካታ ማዕድናት የሚታዩበት ይኸ አውደ ርዕይ ለ5 ቀናት ለሕዝብ ክፍት ሆኖ ይቆያል።
ይኸን የማዕድን እና የቴክኖሎጂ አውደ ርዕይ ያዘጋጀው የኢትዮጵያ የማዕድን ሚኒስቴር ሲሆን በይፋ የተከፈተው አርብ ሕዳር 14 ቀን 2016 ነው።
የማዕድን አምራቾች፣ ወደ ውጪ ላኪዎች ፣ ተጠቃሚዎች፣ የቴክኖሎጅ አምራችና አቅራቢዎች፣ ባለሀበቶች ፣ በዘርፉ የተሰማሩ ግለሰቦች እና ተቋማትም እየተሳተፉ ነው።
የቪዲዮ ዘገባ፦ ሰለሞን ሙጬ
