1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የማዳበሪያ መዘዝ በሐዲያ

ሐሙስ፣ ሐምሌ 20 2015

በአርሶአደሮቹ ላይ እየደረሰ ይገኛል በተባለው እሥርና ወከባ ዙሪያ የዞኑን ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ሃላፊ ሳሙኤል ሽጉጤን ለማነጋገር ጥረት ቢያደርግም ሃላፊው በጉዞ ላይ በመሆናቸው ምላሽ መስጠት እንደማይችሉ ተናግረዋል፡፡በእጅ ሥልካቸው የደወልንላቸው ሌላው የዞኑ ምክትል ዋና አስተዳዳሪ አቶ ፀጋዬ ተረፈ ብንደውልም ጥሪያችንን ሳይመልሱ ቀርተዋል።

Äthiopien | Hadiya Demonstration
ምስል Shewangizaw Wegayehu/DW

«ቀስቅሳችኋል የተባሉት እየታሰሩ ነዉ» ገበሬ

This browser does not support the audio element.

ለደህንነታቸው ሲባል ሥማቸው በዚህ ዘገባ ያልተጠቀሱት አርሶአደር በሃድያ ዞን ሆሳዕና ከተማ አቅራቢ በሚገኘው የጃችቾ ቀበሌ ነዋሪ ናቸው ፡፡ ባለፈው ሰኞ ማዳበሪያ ይቅረብልን በሚል በሆሳዕና ከተማ በተካሄደውና በፖሊስ በተበተነው ሠልፍ መሳተፋቸውን እኝሁ አርሶአደር ይናገራሉ ፡፡ ይህን ተከትሎም እሳቸው የሚኖሩበትን ቀበሌ ጨምሮ በሠልፉ ተሳትፈዋል የተባሉ አርሶአደሮች በፀጥታ አካላት አሥርና ወከባ እየደረሰባቸው እንደሚገኝ ለዶቼ ቬለ DW  ገልጸዋል ፡፡›

ሌላው ሸንቆላ በተባለው ቀበሌ ነዋሪ መሆናቸውንና የሰኞው ሠልፍ ተሳታፊ እንደነበሩ የሚናገሩት አስተያየት ሰጪ በሥም የሚያውቋቸው አርሶአደሮች በፀጥታ አባላት መታሠራቸውን ተናግረዋል ፡፡ “ በቀበሌያችን ማዳበሪ ይቅረብልን ብለን ሠልፉ ከወጣነው መካከል አራርሶ እና ሚሻሞ የተባሉ አርሶአደሮችን ጨምሮ አምስት ሰዎች ታስረዋል ፡፡ አኔ በአጋጣሚ እስከአሁን አልተያዝኩም “ ያሉት እኝሁ አርሶአደር ፖሊሶች በተለይ ሠልፉን አስተባብረዋል ሰዎች ወደ ሆሳዕና ከተማ በመሄድ ማዳበሪያ እንዲጠይቁ ቀስቅሰዋል ያሏቸውን እያሠሩ ይገኛሉ “ ብለዋል ፡፡

ዶቼ ቬለ DW በአርሶአደሮቹ ላይ እየደረሰ ይገኛል በተባለው እሥርና ወከባ ዙሪያ የዞኑን ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ሃላፊ ሳሙኤል ሽጉጤን ለማነጋገር ጥረት ቢያደርግም ሃላፊው በጉዞ ላይ በመሆናቸው  ምላሽ መስጠት እንደማይችሉ ተናግረዋል፡፡በእጅ ሥልካቸው የደወልንላቸው ሌላው የዞኑ ምክትል ዋና አስተዳዳሪ አቶ ፀጋዬ ተረፈ ስብሰባ ላይ መሆናቸውን በመግለጽ ከቆይታ በኋላ እንድንደውል በነገሩን መሠረት መልስን ብንደውልም ጥሪያችንን  ሳይመልሱ ቀርተዋል ፡፡

በደቡብ ክልል የሃድያ ዞን አርሶአደሮች የአፈር ማዳበሪያ ይቅረብልን በማለት ባለፈው ሰኞ በሆሳዕና ከተማ ሠልፍ ማድረጋቸው ይታወቃል ፡፡ ምንም እንኳን ፖሊስ ወደ ሰማይ በመተኮስ ሠልፈኞቹን ቢበትንም ፡፡ ዶቼ ቬለ DW ለሠልፉ ምክንያት ሥለሆነው የማዳበሪያ አቅርቦት ዙሪያ ያነጋገራቸው የዞኑ ህብረት ሥራ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ታደለ ኢጤቦ የአቅርቦት እጥረቱ ሊከሰት የቻለው ዞኑ ለዓመቱ ካቀረበው የማዳበሪያ ፍላጎት መጠን ከግማሽ ያነሰ ብቻ በመላኩ እንደሆነም ገልጸዋል ፡፡ በአሁኑወቅት ከጅቡቲ ወደብ በጉዞ ላይ የሚገኘውን ማዳበሪ በቶሎ ወደየወረዳዎቹ በማድረስ እጥረቱን ለማቃለል ከክልል እና ከፌዴራል ተቋማት  ጋር በትብብር  እየተሠራ እንደሚገኝም ሃላፊው ተናግረዋል ፡፡

ሸዋንግዛው ወጋየሁ

ነጋሽ መሐመድ

ታምራት ዲንሳ

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW