የሜርክልና የሳርኮዚ ዉይይት
ማክሰኞ፣ ነሐሴ 10 2003
ማስታወቂያ
የተለያዩ የዩሮ ተጠቃሚ ሐገራት የገጠማቸዉ ኪሳራና ሌሎች ተመሳሳይ ኪሠራ ይገጥማቸዋል የሚለዉ ሥጋት የዓለምን የገንዘብ ገበያ ክፉኛ እያዋዠቀዉ ነዉ።ከዩሮ ተጠቃሚ ሐገራት ሁሉ በምጣኔ ሐብት አቅም የተሻለ ደረጃ ላይ የሚገኙት የፈረንሳይና የጀርመን መሪዎች የሚደርሱበት ዉሳኔ ችግሩን ለማስወገድ እንደወሳኝ እርምጃ እየተጠበቀ ነዉ።ዛሬ ከቀጥር በሕዋላ ፓሪስ ዉስጥ የተወያዩት ሁለቱ መሪዎች የደረሱበት ዉሳኔ ግን እስካሁን በይፋ አልተነገረም።
ዳንየላ ዩንግሀንስ
ነጋሽ መሀመድ
ተክሌ የኋላ