1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሜርክል ቃል መጠይቅ እና ሩሲያ

ማክሰኞ፣ ሰኔ 7 2014

የጀርመን የቀድሞ መራሒተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ስልጣናቸው ካበቃ ከስድስት ወር በኋላ ሰሞኑን ለመጀመሪያ ጊዜ ለቃለ መጠይቅ ቀርበዋል። እሳቸውም በተለይ ስለ ዩክሬን ወረራ እና በእርሳቸው የስልጣን ዘመን ከሩሲያ ጋር ጀርመን ስለነበራት ግንኙነት ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

Deutschland Altkanzlerin Merkel zu Gespräch im Berliner Ensemble
ምስል Fabian Sommer/dpa/picture alliance

This browser does not support the audio element.

የጀርመን የቀድሞ መራሒተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ስልጣናቸው ካበቃ ከስድስት ወር በኋላ ሰሞኑን ለመጀመሪያ ጊዜ ለቃለ መጠይቅ ቀርበዋል። እሳቸውም በተለይ ስለ ዩክሬን ወረራ እና በእርሳቸው የስልጣን ዘመን ከሩሲያ ጋር ጀርመን ስለነበራት ግንኙነት ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል። በተለይ ከዚህ ጋር በተያያዘ ባለፉት ወራት የተሰነዘረባቸውንም ትችት አንደማይቀበሉ ተናግረዋል። 
በአንጌላ ሜርክል ካቢኔ ውስጥ ኃላፊነት ተቀብለው ይሰሩ የነበሩ ፖለቲከኞች በተለይ ቀደም ሲል ከጀርመን ሩሲያ ግንኙነት ጋር በተያያዘ ስህተት ነበር ብለው ይቅርታ ሲጠይቁ ሜርክል ውይይት እና ውዝግብ ውስጥ ሳይገቡ ከሩቁ ጊዜውን በዝምታ አሳልፈው ነበር። አሁን ግን ብቅ ብለው የተቺዎቻቸውን አስተያየት ውድቅ አድርገዋል። ከዚህም ባለፈ ደግሞ ያለፉት ወራትን በምን መልኩ እያሳለፉ እንደሆነ እና የወደፊት አላማቸውን ሜርክል ተናግረዋል።


ይልማ ኃይለሚካኤል
ልደት አበበ
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW