1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የምሥራቅ ባድዋቾ ወረዳ የመንግሥት ሠራተኞች አድማ

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 6 2016

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሃድያ ዞን የምሥራቅ ባድዋቾ ወረዳ የመንግሥት ሠራተኞች የሥራ ማቆም አድማ መቱ ፡፡ ለሦስት ወራት ወርሃዊ የደሞዝ ክፍያ አለማግኘታቸው ለአድማው መነሾ ምክንያት ነው ተብሏል ፡፡

Infografik Karte Äthiopien AM

በአድማው ከ2 ሺህ በላይ ሠራተኞች መሳተፋቸው ተነግሯል

This browser does not support the audio element.

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሃድያ ዞን የምሥራቅ ባድዋቾ ወረዳ የመንግሥት ሠራተኞች የሥራ ማቆም አድማ መቱ ፡፡ለሦስት ወራት ወርሃዊ የደሞዝ ክፍያ አለማግኘታቸው ለአድማው መነሾ ምክንያት ነው ተብሏል ፡፡ በሥራ ማቆም አድማው የተነሳ ትምህርት ቤቶችና የህክምና ተቋማትን ጨምሮ የመንግሥት አገልግሎት ሰጪ ጽህፈት ቤቶች ተዘግተዋል ፡፡ የሠራተኞቹ ደሞዝ ያልተከፈለው ከአፈር ማዳበሪያ ዕዳ ጋር በተያያዘ በተፈጠረው የፋይናን መቃወስ ነው የሚሉት የአካባቢ ባለሥልጣናት በጉዳዩ ላይ ከሚመለከታቸው ጋር እየተነጋገሩ እንደሚገኙ አስታውቀዋል ፡፡ 

የሥራ ማቆም አድማውን እያደረጉ የሚገኙት በወረዳው የሚገኙ ከ2 ሺህ በላይ ሠራተኞች መሆናቸው ታውቋል ፡፡

ባለፈው ዓርብ በተጀመረውና ዛሬም በቀጠለው የሥራ ማቆም አድማው የተሳተፉት  በወረዳው በተለያዩ መሥሪያቤቶች ውስጥ በማገልገል ላይ የሚገኙ ሠራተኞች መሆናቸው ከአካባቢው የተገኙ መረጃዎች ይጠቁማሉ ፡፡ በወረዳው በመምህርነት እና በህክምና ሥራ ተሰማርተው እንደሚገኙ ለዶቼ ቬለ የተናሩት ሁለት የሥራ ማቆም አድማው ተሳታፊዎችለሦስት ወራት ወርሃዊ የደሞዝ ክፍያ አለማግኘታቸው የአድማው ምክንያት መሆኑን ገልጸዋል ፡፡

ላለፉት ሦስት ወራት ደሞዛቸው እንዲከፈላቸው እየሠሩ ሲጠይቁ መቆየታቸውን የጠቀሱት አስተያየት ሰጪዎቹ " ይሁንእንጂ ለጥያቄያችን ምላሽ የሚሰጥ አካል አላገኘንም ፡፡ በዚህም የተነሳ ሳንበላ በችግር ውስጥ ሥራችንን መቀጠል የለብንም በሚል ከባለፈው ዓርብ ጀምሮ በአንድ ድምፅ ሥራ አቁመን እንገኛለን ፡፡ አሁን ላይ በሥራ ማቆም አድማው የተነሳ ትምህርት ቤቶችና የህክምና ተቋማትን ጨምሮ የመንግሥት አገልግሎት ሰጪ ጽህፈት ቤቶች እንደተዘጉ ይገኛሉ " ብለዋል ፡፡

ዶቼ ቬለ በሠራተኞቹ አድማና በደሞዝ አለመከፍል ዙሪያየምሥራቅ ባድዋቾ ወረዳና የሃድያ ዞን አመራሮችን ለማነጋገር ያደረገው ጥረት አንዳንዶቹ በጉዞ ላይ ሌሎቹ ደግሞ ስብሰባ ላይ መሆናቸውን በመግለጻቸው ሃላፊዎቹን አግኝቶ ምላሻቸውን ማካተት አልተቻልም ፡፡ ያም ሆኖ የምስራቅ ባድዋቾ ወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ብዙአየሁ ሰሎሞን የሠራተኛቹ ደሞዝ ሊከፈል ያልቻለው ከአፈር ማዳበሪያ ዕዳ ጋር በተያያዘነው ነው የሚል መረጃ እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡ የወረዳው መስተዳድር ሠራተኞቹ ደሞዛቸውን አግኝተው ወደ ሥራቸው እንዲመለሱ ለማድረግ ከበላይ የዞን አመራሮች ጋር በመገናኘት ጥረት እያደረገ  እንደሚገኝ አቶ ብዙአየሁ ተናግረዋል ፡፡

የአፈር ማዳበሪያው ዕዳ ከወረዳዎቹ በጀት ሲቀነስ የደሞዝ ወጪን ጭምር በመንካቱ ሠራተኞች በየጊዜው ደሞዝ አልተከፈለንም የሚሉ አቤቱታዎችን እያሰሙ ይገኛሉ ፡፡ ፎቶ፦ ከማኅደር ክምችትምስል Shewangizaw Wegayehu/DW

የቀድሞው የደቡብ ክልል ቀደምሲል የወረዳዎችን መደበኛ በጀት በዋስትና በማሥያዝ የወሰደውን በቢሊየን ብር የሚቆጠር የአፈር ማዳበሪ ዕዳ በወቅቱ ባለመመለሱክልሉን ለበጀት ቀውስ መዳረጉ ይታወሳል ፡፡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ይህ ከፍተኛ ዕዳ አሁን ላይ አዲስ ወደ ተዋቀሩት አራቱ ክልሎች  ተላልፎ ይገኛል ፡፡ የአፈር ማዳበሪያው ዕዳ ከወረዳዎቹ በጀት ሲቀነስ የደሞዝ ወጪን ጭምር በመንካቱ ሠራተኞች በየጊዜው ደሞዝ አልተከፈለንም የሚሉ አቤቱታዎችን እያሰሙ ይገኛሉ ፡፡

ሸዋንግዛው ወጋየሁ

ማተጋፍቶት ስለሺ

አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW