1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የምርምር ዋጋ፣

ረቡዕ፣ ነሐሴ 9 2004

ሴቶች ለዓለም ያበረከቷቸው የፈጠራ ውጤቶች፣ በተለያዩ የሳይንስና ሥነ ቴክኒክ ዘርፎች፤ ጠበብት ከመመራመርና ፤ ለህዝብ ጠቀሜታ ያለው ውጤትም ሲገኝ ፤ ከማቅረብ የተቆጠበቡት ጊዜ የለም። አንዳንዱ የምርምር ውጤት ደግሞ ፍሬው እስኪታይ እጅግ

Bildname: CoRLab-ICub3_Becher Titel: Forschungsroboter ICub Wer hat das Bild gemacht/Fotograf: Presse Universität Bielefeld / CITEC Wann wurde das Bild gemacht?: 2011 Wo wurde das Bild aufgenommen?: CoRLab, Universität Bielefeld Bildbeschreibung: Bei welcher Gelegenheit / in welcher Situation wurde das Bild aufgenommen? Wer oder was ist auf dem Bild zu sehen? Forschungsroboter ICub, lernt durch Nachmachen, verknüpft akustische und visuelle Informationen selbständig zu sinnvollen Zusammenhängen
ምስል Presse Universität Bielefeld / CITEC

አድካሚ ፣በወጪም ረገድ ብዙ ገንዘብ የሚያስከሰክስ መሆኑ የሚታበል አይደለም። የኅዋ ምርምር ፣ በተጨባጭ፤ ለህዝብ ጠቀሜታ የሚያስገኘው መቼ ይሆን!? እውን ሌላ መኖሪያ ፕላኔት ያስገኝልናል? በአጭር ጊዜ መልስ የሚገኝለት አይመስለንም። 

ምስል dpa

ባለፈው ሳምንት ዝግጅታችን፣ 2,5 ቢሊዮን  ዶላር ወጪ ተደርጎባት፣ በቀይዋ ፕላኔት ማርስ ላይ በተሣካ ሁኔታ ስላረፈችው Curiosity ስለተሰኘችው 900 ኪሎግራም ክብደት ያላት ፣ የተንቀሳቃሽ  ቤተ ሙከራ ተግባር ስለምታካሂደው የዩናይትድ እስቴትስ መንኮራኩር  አንድ ዘገባ ማቅረባችን አይዘነጋም። ለነገሩ 2,5 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ተደረገ ተባለ እንጂ ፤ ከየአቅጣጫው የተደረገው ዝግጅትና ርብርቦሽ  ሲታሰብ፤ ከዚያ በላይ ለመሆኑ ከቶ የሚያጠራጥር አይደለም። ከሰማያዊዋ ፕላኔት(ከእኛዋ  ምድር)  ተነስታ ቀይዋ ፕላኔት፤ ማርስ ለመድረስ ፣ ኪዩሬሲቲ 8 ወር ብቻ ነው የወሰደባት ማለትም፣  አንዳንድ የመንኮራኩሯን ዓላማና የተደረገውን የጠበብት ያላሰለሰ ጥረት  ያሰሉ ወገኖች እንደሚሉት፤  ጉዳዩን አቅሎ ማየት እንዳይሆን ያሠጋል። ። መንኮራኩሯን ለመሥራት፣  ጭና የወሰደቻቸው  ፣ የተለያዩ የምርምር መሣሪያዎችን ፤ የተለያዩ መንግሥታት የኅዋ ምርምር መሥሪያ ቤቶች ያደረጉት አስተዋጽዖ ፤ ያ ሁሉ ሲታሰብ ፤ ከሁሉም በላይ ፤ ተልእኮው እንዲሣካ ፤ ከመጠን በላይ ይሠሩ የነበሩ ሳይንቲስቶች(ሴቶችም ፤ ወንዶችም መሆናቸውን አንስተውም)የአነርሱ  ድካም፤ ለምርምራቸው፤ ለትምህርታቸው የተከፈለው ገንዘብም ሁሉ  ሲሰላ ፣  ከይፋው አኀዝ በላይ እንጂ ከዚያ በታች ሊሆን አይችልም።

የማወቅ ጉጉት፤ እንዲሁም ፣  እኔ እበልጥ ፣ እኔ እበልጥ ፉክክር ተጨምሮበት፤« ላም አለኝ በሰማይ» ለመሰለ ፕሮጀክት፣  ይህ ነው የማይባል መጠኑ የበዛ ገንዘብ መከስከስ፣  ባለፉት 50 ዓመታት ገደማ የኅዋ  ምርምር መ/ቤቶች ባሏቸው አገሮች  የታየ ጉዳይ ነው። በዚህ ረገድ የሚደረገው ምርምር ፤ በተለይ ፤ በአሜሪካ፤ በሩሲያ ፣ በቻይና፤ በህንድና በአውሮፓው ኅብረት ቀጣይነት ባለው መልኩ ፤ ወደፊትም መካሄዱ የማይቀር ነው የሚመስለው።

ምስል AP Graphics

ያልታወቀውን ለማወቅ መጣሩ፣ መመራመሩ ፤ ለዚህ የሚያስፈልገውን ወጪ መመደቡም ተገቢ ሊሆን ይችላል። ያም ሆኖ ፣ አልፎ -አልፎ በዚህ ዝግጅት እንዳልነው ፣ እንደምንለው፤ በፀሐይ ዙሪያ  ከሚገኙ ፕላኔቶችና ጨረቃዎች  መካከል፤  እስካሁን በባህርም በየብስም ፤ በአየርም ፤ ህይወት ያላቸው ነገሮች የሚኖሩባት ፕላኔት ፤ ሰማያዊዋ ፕላኔት ፣ ምድራችን ብቻ ናት። ያም ሆኖ ፕላኔታችን  በውስጥዋ ለሚኖሩ ተስማሚ እንደሆነች እንድትቀጥል ፤ በዓለም ዙሪያ ፣  የመንግሥታትና የህዝብ የቤት ሥራ የቱን ያህል ተሠርቷል የሚል ጥያቄ ቢቀርብ አጥጋቢ መልስ የሚሰጥ መኖሩን እንጠራጠራለን!።  በአያሌ ሰው -ሠራሽ ችግሮች፣ በአየር ብክለትና በደን ምንጠራ፤ በሰሜንና  ደቡብ የምድር ዋልታዎች  የበረዶ ክምር መናድና መቅለጥ ሳቢያ ፣ ዓለማችን  ከዓመት ዓመት ፤ ሙቀቷ እየጨመረ ፣ ምድረ በዳ እየተስፋፋ ፤ የውቅያኖስ  የባህር ልክም ከፍ እያለ በመሄድ ላይ  መሆኑ እሙን ነው። አሁን፣  7 ቢሊዮን ገደማ ኑዋሪዎች የሚገኙባት ምድር ፤ ለዘለቄታው የኑዋሪዎቿን  ህይወት መደገፍ ይቻላት ዘንድ ፤ ሲሆን አሸዋ የሸፈናቸው ምድረ-በዳዎችን በመስኖ ውሃ እንደገና አረንጓዴ እንዲሆኑ ማብቃት፣ ያም እንኳ  ቢቀር፣ ድርቅ ይበልጥ እንዳይስፋፋ መላ መሻቱ ላይ የቱን ይህል ተተኩሯል?

ምስል dpa

ባለፉት ዘመናት፣ ለሥልጣኔ መስፋፋት ፣ ለማኅበራዊ ኑሮ ችግሮች መቃለል፤ ጠቀሚ ግኝቶችን ካስመዘገቡት ውስጥ በጾታ ነጥለን  ስናየው አብዛኞቹ ወንዶች  ይሁን እንጂ፣ ዐቢይ ትርጉም የሚሰጣቸውን የሥነ ቴክኒክ የፈጠራ ውጤቶች ያቀረቡት ሴቶች ቁጥር ቀላል አይደለም። በጣም ጠቀሚ የሚባሉ ግኝቶችን ለህዝብ ጠቀሜታ እንዲውሉ ካደረጉት መካከል  46 የሚሆኑት በምርምር ውጤታቸው፤ ይበልጥ የጎላ ስም አላቸው። ከእነዚህ ውስጥ ደግሞ 10ሩ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ናቸው። ግኝታቸውም በቀጥታ ለአስፈላጊ ጉዳዮች የዋሉ መሆናቸው የታወቀ ነው። በትውልድ ፖላንዳዊት የሆኑት፤ እ ጎ አ፣ ኅዳር 7 ቀን 1867 በወርሶ የተወለዱት ፣  ኔ ማሪያ እስክሎዶቭስካ ፣  በኋላ Marie Kurie  የሚል ስም የያዙት ሴት ተመራማሪ ፣ ቀዳሚውን ቦታ ይይዛሉ።  እ ጎ አ  በ 1891 የፊዚክስና ሂሳብ ትምህርታቸውን ለመቀጠል ወደ ፓሪስ፣  ሶርቦን ዩንቨርስቲ የተጓዙት ፣ማሪ ኩሪ፣ በሳይንሱ ዓለም የሚታወቁት፤ በሥነ-ቅመማና በፊዚክስ ባደረጉት ሰፊ ምርምር ነው። በምርምራቸውም ለመጀመሪያ ጊዜ፤ በ 1903፣ በፊዚክስ ከባላቸው ፣ ፒዬር ኩሪ ጋር ከፊሉን የኖቤል ሽልማት ለመቀበል በቅተዋል። ቀሪውን ግማሽ ሽልማት ያገኙት፤ በ 1896 አደገኛ ጨረርን፤ (RADIOACTIVITY)ን ያገኙት  ኦንሪ ቤክሬል  ናቸው።  

 ማሪ ኩሪ፣ በምርምር ኖቤል ሽልማት ለማግኘት  የመጀመሪያቱ ሴት ሳይንቲስት ነበሩ። በ 1906 ባላቸው ፒዬር ኩሪ ሲሞቱ ፤ እርሳቸው ትምህርታቸውን በተከታተሉበትና የዶክትሬት ማዕረግ ባገኙበት በፓሪሱ የሶርቦን ዩንቨርስቲ፣ በሳይንስ ፋክልቲ፤ የአጠቃላይ ፊዚክስ ፕሮፌሰር ሆኑ፤። በዚያ  ዘመን ፈረንሳይ ውስጥ፣  አንዲት ሴት ከተጠቀሰው ደረጃ ስትደርስ ፣ ማሪ ኩሪ የመጀመሪያቱ ነበሩ። የኩሪ ቤተ-ሙከራ ዋና ሥራ አስኪያጅ እንዲሆኑም ያኔ ነበረ የተመረጡት።

ተክሌ የኋላ

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW