የምርጫ ቦርድና ተቃዋሚዎች መንግስትን ወቀሱ
ማክሰኞ፣ የካቲት 16 2013
ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ ለመጪዉ ምርጫ በሚያደርገዉ ዝግጅት የፌደራልና የክልል መንግስታት ባለስልጣናት ትብብር እንደነፈጉት አስታወቀ። የምርጫ ቦርድ ባለስልጣናት ዛሬ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ተወካዮች ጋር ባደረጉት ዉይይት እንደገለፁት በየደራጃዉ የሚገኙ ባለስልጣናት ቦርዱ የሚፈልጋቸዉን ፅሕፈት ቤቶች እና የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት ዳተኞች ናቸዉ።የቦርዱ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚዴቅሳ፣ ባለስልጣናት ቦርዱን ካልተባበሩ የምርጫዉ ሒደት ሊደናቀፍ እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካዮችም ቅሬታቸዉን ገልፀዋል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ነጋሽ መሐመድ
ኂሩት መለሰ