1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ሀገራዊ ምርጫ ማራዘሙን በቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል የምንቀሳቀሱ ተቃዋሚ የፖሊቲካ ፓርቲዎች ይደግፋሉ

ማክሰኞ፣ መጋቢት 29 2012

የቦሮ ዴሞክራቲክ ፓርቲ ምርጫ ቦርድ የጊዜ ሰሌዳውን ሲያራዝም ከተቃሚዎች ጋር መመካከር እንደነበረበት በመግለጽ ከመስከረም በኃላ የሽሽግር መንግስት እንዲመሰረት እንፈልጋለን ብለዋል፡፡ ዓለም ስለኮሮና በሚጨነቅበት በዚህን  ወቅት የክልሉ መንግስት ተቃዋሚ ፓርቲዎችን  እያሰረ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

Äthiopien Logo Boro Democratic Party
ምስል፦ Boro Democratic Party

ከመስከረም በኃላ የሽሽግር መንግስት እንዲመሰረት እንፈልጋለን

This browser does not support the audio element.

ከመስከረም በኃላ የሽሽግር መንግስት እንዲመሰረት እንፈልጋለን 
የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ  በኮሮና ቫይረስ ምክንት ሀገራዊ ምርጫ ማራዘሙን በቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል የምንቀሳቀሱ ተቃዋሚ ፖሊቲካ ፓርቲዎች እንደሚደግፉ አስታወቁ፡፡ ከተቃዋሚዎች አንዱ የሆነው የቦሮ ዴሞክራቲክ ፓርቲ ምርጫ ቦርድ የጊዜ ሰሌዳውን ሲያራዝም ከተቃሚዎች ጋር መመካከር እንደነበረበት በመግለጽ ከመስከረም በኃላ የሽሽግር መንግስት እንዲመሰረት እንፈልጋለን ብለዋል፡፡ ዓለም ስለኮሮና በሚጨነቅበት በዚህን  ወቅት የክልሉ መንግስት ተቃዋሚ ፓርቲዎችን  እያሰረ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን በበኩሉ ታሰሩ የተባሉ ሰዎች ግጭት በመቀስቀስ ተጠርጥረው እንደሆነ  ጠቁመዋል፡፡ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከምንቀሳቀሱ ተቃወሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የቤኒሻንጉል ህዝቦች ነጻነት ንቅናቄ፣ የቦሮ ዴሞክራቲክ ፓርቲ እና የጉሙዝ ህዝብ ዴሞክረሲያ ንቅናቄ ለብሐራዊ ምርጫ ቢርድ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት  ምርጫ ማራዙን ቢደግፉም መሟላት የነበረበት ቅድመ ሁኔታዎች ነበሩ ይላሉ፡፡ የቦሮ ድሞክራቲክ ፓርቲ ሀሳቡን ከሚደግፉት መካከል አንዱ ሲሆን ብሐራዊ ምርጫ ቦርድ ተቃዋሚ ፓለቲካ ፓርቲዎች ማወያየት ነበርበት ብለዋል፡፡ የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ አመንቴ ገሺ ህጋዊ የሆነው መንግስት የስልጣን ዘመኑ ካለፈ በኃላም የሽግግር መንግስት መመስረት እንዳለበት ተናግረዋል፡፡ በሌላ በኩልም በክልሉ ውስጥ በህጋዊ መንገድ ተደራጅተው በሚቀሳቀሱ የተቃወሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ላይ የክልሉ መንግስት እስራትና ወከባ በመፍጠር ጫና እያሳደረ ነውም ብለዋል፡፡ ለአብነትም የቤህኔን እና የሶስቱ ደርጅቶች ጥምር ፓርቲ ሊቀመንር የሖኑት  አቶ አብዱል ሰላም ሸንገል ባለፈው ሳምንት ሐሙስ  መታሰራውን ገልጸዋል፡፡የቤኒሻንጉል ህዝቦች ነጻነት ንቅናቄ ድርጅት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሐሊል ሙሳል በበኩላቸው የምርጫ ቦርድ ውሰኔን ተገቢ ነው ብለዋል፡፡ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ቅዲሚያ መስጠት ያለብን ለፖለቲካ ሳይሆን በዓለምን ዓቀፍ ደረጃ እየተሰራጨ የሚገኘውን የኮሮና ቫይረስን መከላከል መሆን እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡ የጉሙዝ  ህዘብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄም እንዲሁው  የምርጫ መራዘም  ትክክለኛ ውሳኔ ነው ብለዋል፡፡ የድርጅቱ ሓላፊ አቶ ግራኝ ጉዴታ  ለኮሮና መፍትሄ እስካልተገኘ ድረስ ምርጫ ማድረግ ህብረተሰቡ ለቫይረሱ ይበልጥ ተጋለጭ  ስለሚሆን መራዘሙ ተገቢ  እንደሆነ ተናግረዋል፡፡የቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኃላፊ ኮሚሽነር መሐመድ አምደኒል  በክልሉ ውስጥ ታሰሩ ስለ ተባሉ የቤኒሻንጉል ህዝቦች ንቅናቄ ሊቀመንበር አቶ አብዱል ሠላም ሸንገል ጉዳይ ተጠይቀው  ባሁኑ ወቅት በሀገር ዓቀፍ ደረጃም ሆነ በክልሉ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ሲባል የተከለከሉ ህጎችን በመጣሳቸው እና  የድርጅታቸውን አባላት ሰብስቦ በማወያየታውና  ህዝቡን ለግጭት በማነሳሳት ወወንጀል ተጠርጥረው መታሰራቸውን ገልጸዋል፡፡ሶስቱም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ተቋዋሚ ፖሊተካ ፓርቲ መሪዎች ከሁለት ወር በፊት ታስረው እንደበረ መዘገባችን የሚታወስ ነው፡፡ አቶ አብዱል ሰላም ሸንገልም ባለፉት አራት ወራት ውስጥ  ለሶስተኛ ጊዜ ባፈው ዓሙስ እንደተሳሩ ከፓርቲው የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ምስል፦ DW/N. Dessalegn

ነጋሳ ደሳለኝ

ታምራት ዲንሳ

አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW