1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

 የምስራቅ ወለጋ ተፈናቃዮች አቤቱታ

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 12 2014

የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች በስፍራው በብዛት መንቀሳቀስ ቢጀምሩም ወረዳውን ከሌላ አካባቢዎች ጋር የሚያናኙ መንገዶች አሁንም አልተከፈቱም ብለዋል፡፡ ለታመሙ ሰዎችና ለወላድ እናቶች የተለያዩ መድሀኒትና የህኪምና ድጋፎችንም ለመስጠት አዳጋች ሆነው መቆየቱን ጠቁመዋል፡፡

Infografik Karte Äthiopien EN

የምሥራቅ ወለጋ ተፈናቃዮች

This browser does not support the audio element.

በምስራቅ ወለጋ ኪራሙና እና ጊዳ አያና ወረዳዎች ከመስከረም 2014 ዓ.ም ወዲህ ከ80ሺ በላይ ሰዎች መፈናቃላቸውን ከየወረዳው  የተገኘ መረጃ ያመለክታል፡፡ በተለይም በኪራሙ ወረዳ ስር በሚገኙ 11 በሚደርሱት ቀበሌዎች ውስጥ የሚኖሩ ዜጎች ተፈናቅለው በከተማዋ ተጠልሎ እንደሚገኙ ያነጋርናቸው ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡ የተፈናቀሉ ዜጎች ሰብአዊ እርዳታ ባለፈው 2 ወራት እንተቋረጠባቸውም ነግረውናል፡፡  የኪራሙ ወረዳ የኮሙኒኬሽን የስራ ሂዴት የሆኑት አቶ ፍቃዱ  አያና  ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚደርሱ ድጋፍች አነስተኛ እንደነበሩ ገልጸው  ድጋፍ የተቋጠባቸውን መጠለያዎች በመለየት ችግሩ እንዲቀረፍ ጥረት ይደረጋል ሲሉ ለዲዳቢሊው ተናግረዋል፡፡ የጊዳ አያና ወረዳ  የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኃላፊ አቶ ደረጀ ደበሎ  በወረዳቸው በበተሰብ ደረጃ 12577 ዜጎች ተፈናቅለው እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡
በመስከረም ወር 2014 ዓ.ም መጨረሻ በኪራሙ ወረዳ ሀሮ ከተባለች ስፍራ ተፈናቅለው በወረዳው ከተማ እንደሚገኙ የተናገሩት አቶ አብዲ ተማም እስካሁን 2 ጊዜ ብቻ ድጋፍ እንደደረሳቸው ገልጸዋል፡፡ ወደ ነበሩት ሐሮ ለመመለስ በስፍራው የጸጥታ ሁኔታ አስጊ በመሆኑን መመለስ አለመቻላቸውን የተናገሩ ሲሆን ቀድሞ ከነበሩት  ከ10 በላይ የቁም እንስሳት እንተወሰደባቸወም አብራርተዋል፡፡ ከትናንት በስቲያም ከሌላ ቦታ የመጡ ተባሉና ከአካባቢው የተደራጁ ሰዎች የቁም እንስሳት መዝረፋቸውን እና በሰዎች ላይም ጉዳት ማድረሳቸውን አክለዋል፡፡ 
በኪራሙ ወረዳ ቦቃ በተባለች ስፍራ የተፈናቀሉ ሌላው ነዋሪ እንደተናገሩት ደግሞ ሰብአዊ እርዳታ ከመቋረጡ ውጪ የጸጥታ ሁኔታ በፊት ከነበረው መሻሻል አሳይቷል፡፡ የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች በስፍራው በብዛት መንቀሳቀስ ቢጀምሩም ወረዳውን ከሌላ አካባቢዎች ጋር የሚያናኙ መንገዶች አሁንም አልተከፈቱም ብለዋል፡፡ ለታመሙ ሰዎችና ለወላድ እናቶች የተለያዩ መድሀኒትና የህኪምና ድጋፎችንም ለመስጠት አዳጋች ሆነው መቆየቱን ጠቁመዋል፡፡
የኪራሙ ወረዳ የኮሙኒኬሽን ጽ/ ቤት የስራ ሂዴት መሪ የሆኑት አቶ ፈቃዱ አያና በወረዳቸው የተፈናቀሉ ዜጎች ቁጥር 70ሺ በላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ሰብአዊ ድጋፍ በመንግስትም ሆነ በግል ተቋማት ለተፈናቀሉ ዜጎች ሲደርስ መቆየቱን ገልጸው የመጡ ድጋፎች በቂ እንዳልነበሩ አብራርተዋል፡፡ከትናንት በስቲያ በቡረ በኩል ተሻገሩ ያሉት ታጣቂዎች በኪራሙ ወረዳ ቡረቃ ሶሮማ የሚትባል ቀበሌ ውስጥ በሰዎች ላይ ጥቃት ማድረሳቸውንና ሰዎች መፈናላቸውንም አመልክተዋል፡፡
"ባለፉት አምስትና ስድስት ወራት የተፈናሉት 73ሺ የሚደርሱ ሰዎች በኪራሙ ከተማ ነው የሚገኙት፡፡ ሰብአዊ ድጋፍ ለማዳረስ ጥረት አድርገናል ነገር ግን  በቂ አይደለም፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ  ሸነ የተወሰኑ አካባቢዎችን ሲለቅ ከባድ መሳሪያ ሲናይፐርን ጨምሮ የታጣቁ ከጎጃም የተሻገሩ ሀይሎች  በዚሁ በኪራሙ ወረዳ ቡርቃ ሶሮማ በሚባል ቀበሌ ውስጥ ብቻ 97 ከብቶች ነድተዋል፡፡ አምስት ሰዎች ደግሞ ተገድለዋል፡፡ የተወሰኑ ሰዎች አሁንም ተፈናቅለው ይገኛሉ፡፡ ይሄ በአንዱ ቀበሌ የተከሰተ  ሲሆን የወረዳው በሙሉ ሲጣራ ደግሞ ከዚህ በላይ ሊሆን ይችላል፡፡"  የተፈናቀሉ ዜጎችን ለማገዝ ተጨማሪ ድጋፍ ክልል እንደሚላክም ተናግረዋል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ከምስራቅ ወለጋ ዞኑንና ከኦሮሚያ ክልል የጸጥታ ዘርፍ ኃላፊዎች ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት ያደረኩት ጥረት ስልካቸውን ባለማንሳታቸው ማግኘት አልተቻለም፡፡

ነጋሳ ደሳለኝ

ነጋሽ መሐመድ

እሸቴ በቀለ

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW