የምክር ቤት ምርጫ በእሥራኤል
ማክሰኞ፣ መጋቢት 8 2007ማስታወቂያ
የሕዝብ አስተያየት መለኪያዎች ማጠቃለያ እንዳመለከተው ከሆነ ተቃዋሚው የጽዮናውያን ኅብረት ከአራት መቀመጫዎች ሦስቱን በማግኘት ከገዢው ሊኩድ ፓርቲ እንደሚልቅ ተተንብዮዋል። የሊኩድ ፓርቲ መሪው ጠቅላይ ሚንሥትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ከወዲሁ ስጋት የገባቸው ይመስላል። ስቱዲዮ ከመግባቴ በፊት የእሥራኤሉ ወኪላችን ጋዜጠኛና ደራሲ ዜናነህ መኮንንን አነጋግሬዋለሁ። መራጩ ሕዝብ በአብዛኛው የኢኮኖሚ ጥያቄ ቢያቀርብም ፖለቲከኞች ግን ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ማድረጋቸውን ዜናነህ ጠቅሷል። የእስራኤል ምርጫን በተመለከተ የመገናኛ ብዙኃን እና የኢትዮጵያ ቤተ-እሥራኤላውያንን ጨምሮ የሕዝቡ አስተያየት ብሎም ሚናው ምን እንደሚመስል በማብራራት ይጀምራል።
ዜናነህ መኮንንን
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ተክሌ የኋላ