የምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን መግለጫ
ረቡዕ፣ ጥቅምት 25 2013
ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በተልዕኮ ላይ እያለ ትናንት ዕኩለ ሌሊት ላይ በትግራይ ልዩ ኃይል የደረሰበት ጥቃት «ከባዕድ ወረራ የከፋ የከሃዲነት ርምጃ ነው» ሲሉ ክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ተናገሩ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በሰጡት መግለጫ በዛሬው ዕለት ልዩ ኃይሉን በማንቀሳቀስ በአማራ ሕዝብ ላይ ወረራ ለማካሄድ ከፍተኛ ርብርብ በማካሄድ ላይ ይገኛል ብለዋል። ለዚሁ ወቅታዊ ጉዳይ ሲባል አዲስ የተቋቋመው የተግባቦት ኮሚቴ ቃል አቀባይ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን «ግጭቱ በአንድ ቤተሰብ መሀከል የሚደረግ መኾኑ ቢያሳዝንም ህግ የማስከበር ሥራ የግድ ነው» ብለዋል። «ይኼ ግጭት በትግራይ ሕዝብ እና በተቀረው የኢትዮጵያ ሕብዝ መካከል አይደለም» ሲሉም አክለዋል። ትግራይ ውስጥ የኢንተርኔት እና የስልክ አገልግሎት በመቋረጡ ከትግራይ በኩል አስተያየት ለማካተት አልቻልንም። ሰለሞን ሙጬ ዝርዝር ዘገባ አለው።
ሰለሞን ሙጬ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
እሸቴ በቀለ