1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የሞት ቅጣት ያስቀጣል የተባለው የታንዛኒያ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪው ክስ

ቅዳሜ፣ ግንቦት 2 2017

ቻዴማ የተባለው የታንዛኒያ ዋና ተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ቱንዱ ሊሱ ባለፈው ወር ባደረጉት ንግግር ፤ ታንዛኒያውያን እንዲያምፁ እና የአገሪቱን ፕሬዚዳንታዊ እና የፓርላማ ምርጫ እንዲረብሹ አድርገዋል ተብለው በቁጥጥር ስር ውለዋል። ቲንዱ የተከሰሱት በሀገር መክዳት ሲሆን፤የሞት ቅጣት ይጠብቃቸዋል ተብሏል።

ቲንዱ ሊሱ፤ የታንዛኒያ የተቃዋሚው ፓርቲ የቻዴማ መሪ በቁጥጥር ስር ሲውሉ።
ቲንዱ ሊሱ፤ የታንዛኒያ የተቃዋሚው ፓርቲ የቻዴማ መሪ በቁጥጥር ስር ሲውሉ።ምስል፦ Emmanuel Herman/REUTERS

የሞት ቅጣት ያስቀጣል የተባለው የታንዛኒያ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪው ክስ

This browser does not support the audio element.

የታንዛኒያ ዋና ተቃዋሚ መሪ ቱንዱ ሊሱ የሞት ቅጣት ይጠብቃቸዋል ተብሏል። ፓርቲያቸው ክሱ መሰረታዊ የምርጫ ማሻሻያ እንዲደረግ ዘመቻ ከከፈቱ በኋላ የመጣ እና ከፖለቲካ ጋር የተያያዘ ነው ብሏል።ቻዴማ የተባለው የታንዛኒያ ዋና ተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ቱንዱ ሊሱ ባለፈው ወር ባደረጉት ንግግር ፤  ታንዛኒያውያን እንዲያምፁ እና የአገሪቱን ፕሬዚዳንታዊ እናየፓርላማ ምርጫ እንዲረብሹ አድርገዋል ተብለው በቁጥጥር ስር ውለው በሀገር ክህደት ተከሰው ነበር።ቻዴማ የምርጫውን "የሥነ ምግባር ደንብ" ለመፈረም ፈቃደኛ ባለመሆኑ ከምርጫው ተወግዷል።ሊሱ በአገር ክህደት ከተከሰሱ የሞት ቅጣት ይጠብቀቸዋል።በምስራቅ አፍሪቃ የሀገር ክህደት ወንጀልን ለፖለቲካ ዓላማ ማስፈፀሚያ ማዋል  ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል ይላሉ።

በሀገሪቱ የንግድ ከተማ በሆነችው ዳሬሰላም የህግ ባለሙያ የሆኑት ፉልጀንስ ማሳዌ።
«እንደ የኮመንዌልዝ አካል ለታንዛኒያ በጣም ከባድ ነው ። ለዚህም ነው እንደዚህ አይነት ወንጀሎች በፖለቲከኞች እና በተቃዋሚዎች በሚሰጡ የፖለቲካ መግለጫዎች ላይ ያነጣጠሩት።»ማሳዌ እንደሚሉት ክሱ ክብደት ቢኖረውም ሊሱ፤ ፍርድ ቤት በግልጽ ከቀረቡ በእሳቸው ላይ የተከፈተውን ክስ ለመከላከል  ዝግጁ መሆናቸውን  ግልጽ አድርጓዋል።ባለሥልጣናቱ ግን ከእስር በቪዲዮ እንደሚካሄድ ሲናገሩ ግን ችሎት ላይ ለመታደም ፈቃደኛ አልሆኑም።«ደንበኞቻችን ፍርድ ቤት መቅረብ መብታቸው ነው። በወንጀል ክስ ፍርድ ቤት ከተጠራህ  በአካል መቅረብ አለብህ። በወንጀል ጉዳይ፣ ቤትህ ወይም ሌላ ቦታ ሆነህ መዳኘት አትችልም። ደንበኛችንም ህጉን ስለሚያውቅ በበይነመረብ ለመከታተል ፈቃደኛ አልሆነም።» ብለዋል።

የታንዛኒያ ፖሊስ የተቃዋሚ ፓርቲ የቻዴማ ደጋፊዎችን የፓርቲው መሪ ከታሰሩ ወዲህ ማዋከብ ጀምሯል።ምስል፦ Emmanuel Herman/REUTERS

በታንዛኒያ ለምርጫ ማሻሻያ የሚደረግ ትግል 

ሊሱ በደቡባዊ ታንዛኒያ በቁጥጥር ስር የዋሉት ለገዥው ፓርቲ ያደላል ያሉትን የሀገሪቱ የምርጫ ስርዓት ላይ ከፍተኛ ማሻሻያ እንዲደረግ የሚጠይቅ የፓርቲያቸውን «ማሻሻያ ከሌሌ ምርጫ የለም»/Reforms, No Elections/ ዘመቻ ለማስተዋወቅ ህዝባዊ ስብሰባዎችን ሲያካሂዱ ነበር። 
መንግስት በምርጫ እንዳይሳተፉ ዜጎችን ማበረታታት ከአመፅ ድርጊት ጋር እኩል ነው ይላል።የቻዴማ ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት ጆን ሄቼ በተደጋጋሚ ለእስር ተዳርገዋል። ነገር ግን ምንም አይነት ክስ ሳይመሰረትባቸው ተለቀዋል።የሀገሪቱ መስራች ወጣቶችን ያበረታቱት ለፍትሃዊ ዓላማ መቆምን ነው ይላሉ።

«ሙዋሊሙ ኔሬሬ /የመጀመሪያው የታንዛኒያ ፕሬዝዳንት/ እንዳለው፤ የታንዛኒያ ወጣቶች በጨቋኝ ስርዓት ላይ ማመፅ አለባቸው። ምርጫን በሚሰርቁ ሰዎች ላይ ማመፅ፣እና ምርጫ መሰረቁን መቃወም ችግሩ ምንድን ነው?»ብለዋል።
አንጋፋው ጠበቃ እና ጋዜጠኛ ጄኔራሊ ኡሊምዌንጉ የሄቼን ሀሳብ አስተጋብተዋል።ለDW እንደተናገሩት ከረዥም ጊዜ ጥረት በኋላ ዲሞክራሲን ለመገንባት የሞከረችው ታንዛኒያ፤ በአንድ ወቅት የጎረቤቶቿን ሰላም ለማስጠበቅ የምትታወቅ ነበረች። አሁን ግን የተገኘውን ትንሽ እድገት ለመቀልበስ እርምጃዎችን እየወሰደች ነው።በማለት ገልፀዋል።ኡሊምዌንጉ እንዳሉት መንግስት እውነተኛ ምርጫ ከማካሄድ እና አፈፃፀሙን ከማሳየት ይልቅ፤ የተጋነነ አሸናፊነትን በመቶኛ ለማወጅ ወስኗል።እንደ ኡሊምዌንጉ  በታንዛኒያ በጎርጎሪያኑ 2019፣ 2020 እና ያለፈውን ዓመት የተካሄደውን የአካባቢ አስተዳደር ምርጫ ጨምሮ «እውነተኛ ምርጫዎች» አልነበሩም።

የታንዛኒያ የተቃዋሚው ፓርቲ መሪ ቲንዱ ሊሱ በቁጥጥር ስር የዋሉት የምርጫ ደንብን የሚያጣጥል ንግግር አድርገዋል ተብለው ነው።ምስል፦ Emmanuel Herman/REUTERS

ተቋማት የሊሱን እስራት አውግዘዋል

ለፖለቲካዊ ነፃነት፣ ለግል ነፃነት፣ ለእኩልነት ዕድል እና ለኢኮኖሚ ልማት የሚሟገተው ዓለም አቀፍ ዲሞክራሲያዊ ህብረት (አይዲዩ) በሚያዝያ ወር መጨረሻ ላይ መግለጫ አውጥቷል። በኤምቢንጋ ከተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ ጋር በተያያዘ የሊሱ «የቀጠለው እስራት እና የፖለቲካ ስደት በእጅጉ አሳስቦኛል»ብሏል።አይዲዩ «የምርጫ ማሻሻያ እና ነፃ ምርጫን መጠየቅ የአገር ክህደት አይደለም- የዲሞክራሲ ዋናው ነገር ነው» ሲል ሊሱ በአስቸኳይ እና ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ እና የቻዴማ ሙሉ የፖለቲካ ተሳትፎ መብቶች እንዲመለሱ ጠይቋል።
የአለም አቀፉ የህግ ባለሙያዎች ኮሚሽን (ICJ) በተመሳሳይ መግለጫ የታንዛኒያ መንግስት የህግ የበላይነትን መጣስን እንዲያቆም ጠይቋል። 
«በብሔራዊ፣ ክልላዊ እና ዓለም አቀፋዊ ሕግ በተደነገገው መሠረት የፖለቲካ ፓርቲዎች የመደራጀት እና የመቀስቀስ መብቶችን ማክበር እና የታንዛኒያ ሕዝቦች በነፃነት የመደራጄት እና የመሰብሰብ መብቶችን ማክበር ያስፈልጋል።» ብለዋል።  

ኮሚሽኑ፤ የታንዛኒያ የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዝዳንት ሳሚያ ሱሉሁ ሀሰን ጥሩ የአመራር ስልት እንዲከተሉ እና ወደ ስልጣን ሲመጡ ሀገሪቱን ወደ ዲሞክራሲያዊ እድገት ለመምራት የገቡትን ቃል እንዲያድሱ ጠይቋል።የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች የታንዛኒያ መንግስት በተቃዋሚዎች ላይ የሚወስደውን ርምጃ ኮንነዋል።አምነስቲ ኢንተርናሽናል የሊሱን እስራት በማውገዝ በመንግስት የተካሄደውን «የጭቆና ዘመቻ» አውግዟል፣ «ተቺዎችን ዝም የማሰኘት የከባድ እጅ ስልቶች» ሲል ተችቷል። መንግስት ትችቱን ውድቅ አድርጓል።የኪሱቱ ፍርድ ቤት ለግንቦት 19 ቀጠሮ ሊሱ ጉዳያቸውን በአካል አቀርበው እንዲሰሙ የማረሚያ ቤቱን ባለስልጣናት አዟል።
ፍሉገንቴ ማሳዌ ግን ክሱ ይቋረጣል ባይ ናቸው።«ይህ ጉዳይ በፖለቲካዊ መልኩ እንደሚቋረጥ እርግጠኛ ነኝ። ልክ ለአንድ አመት ያህል ታስሮ እንደተለቀቀው ምቦዌ። ከሁሉም በላይ ሊሱን የሚጎዳው ክሱ ውድቅ እስኪደረግ ወይም ፍርድ ቤቱ  ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ የሚታሰርበት ጊዜ ነው።» ብለዋል።


ፀሀይ ጫኔ
ማንተጋፍቶት ስለሺ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW