1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የሞዴል ቀነኒ አዱኛ ኅልፈትና ስርዓተ ቀብር

ሥዩም ጌቱ
ረቡዕ፣ መጋቢት 3 2017

የኦሮምኛ ሙዚቃ ታዋቂ አቀንቃኝ አርቲስት አንዱኣለም ጎሳ ፍቅረኛ የሞዴል ቀነኒ አዱኛ ስርዓተ ቀብር ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጸመ ። በሞዴል ሥራዋ እጅግ የሚትታወቀው ቀነኒ ከፍቅረኛዋ ጋር ከሚኖሩበት መኖሪያ ቤት ትናንት ንጋት አከባቢ ከማለዳው 10 ሰዓት ግድም ከአምስተኛ ፎቅ ወለል ወድቃ ሕይወቷ ማለፉ ተነግሯል ።

Beisetzung der äthiopischen Model Keneni Adugna in Addis Abeba
ምስል፦ Seyoum Getu/DW

ፖሊስ ያልተረጋገጡ መረጃዎች እንዳይሰራጩም አሳስቧል

This browser does not support the audio element.

የኦሮምኛ ሙዚቃ ታዋቂ አቀንቃኝ አርቲስት አንዱኣለም ጎሳ ፍቅረኛ የሞዴል ቀነኒ አዱኛ ስርዓተ ቀብር ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጸመ ። በሞዴል ሥራዋ እጅግ የሚትታወቀው ቀነኒ ከፍቅረኛዋ አርቲስት አንዱዓለም ጎሳ ጋር ከሚኖሩበት መኖሪያ ቤት ትናንት ንጋት አከባቢ ከማለዳው 10 ሰዓት ግድም ከአምስተኛ ፎቅ ወለል ወድቃ ሕይወቷ ማለፉ ተነግሯል ። ፖሊስ በወቅቱ አብሯት የነበረውን አርቲስት አንዱዓለም ጎሳን በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ እያከናወንኩ ነው ብሏል ። ዛሬ በቅድስት ሥላሴ በተፈጸመው ስርዓተ ቀብሯ ላይ ፍቅረኛዋ አርቲስት አንዱኣለም ጎሳ በፖሊሶች በመታጀብ ተገኝቶ እርሙን በማውጣት ስርዓተ ቀብሯ ላይ ተገኝቷል፡፡

ትናንት ማለዳውን ኅልፈቷ የተሰማው የአርቲስት አንዱዓለም ጎሳ ፍቅረኛ የሞዴል ቀነኒ አዱኛ ስርዓተ ቀብር ዛሬ ከሰዓቱን በአዲስ አበባ ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ስፈጸም በርካታ አድናቂዎቿ፣ ቤሰብ፣ ጓደኞቿ ተገኝተው መሪር ሐዘናቸውን ገልጸዋል፡፡ ትናንት በድንገት የተሰማው የወጣቷ ኅልፈት በርካቶችን በማኅበራዊ መገኛኛ በኩልም በማስቆጣት ለፍትህም ሲጣሩ ተስተውሏል፡፡
ዛሬ በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የቀብር ስነስርዓት ከተፈጸመ በኋላ የሟ አባት አቶ አዱኛ ዋቆ ለቀስተኞች ፊት ባስተላለፉት መልእክታቸው ልጃቸውን ፍትህ በእጅጉ እንደሚሹ አሳውቀዋል፡፡ “ሁላችበሁንም የምጠይቃችሁ፤ አርቲስቶቻችንም ለናንተ የማስተላልፈው መልእክት የልጄን እውነት አፈላልጉኝ፡፡ እንደ ሃጫሉ ሞትም ተድበስብሶ እዳይቀርብኝ፡፡ እኔ ለማስተማር ነበር ከእቅፌ ያወጧሃት እንጂ እንዲህ እንድትቀጠፍብኝ አልነበረም፡፡ ሌላ የምለውም የለም” ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

የሞደል ቀነኒ አዱኛ አባት አቶ አዱኛ ዋቆ አክለውም በተለይም ለዶቼ ቬለ በሰጡት አስተያየታቸውን፤ “እኔ ቀነኒን የማውቃት እጅግ ታታሪ፣ ስራን የምትፈጥር፣ ደግሞም ሥራ አክባሪ ናት፡፡ እንዲህ እርኩስ መንፈስ ይዟት እራሷን ታጠፋለች የሚለውን ውሸት ነው የምለው፡፡ እሷ ስቸግርህ ተበድራ እንኳ የምትሰጥ እንጂ ከሷ ይህ አይጠበቅም” በማለት በልጃቸው ኅልፈት መሪር ሐዘናቸውን ገልጸዋል፡፡

እናም አሉ የሟቿ ተስፈኛ ወጣት አባት አቶ አዱኛ ዋቆ፤ “እኔ አሁንም ቢሆን የፍትህ አካላት ተከታትለው፤ ሀቋን ያውጣልኝ ነው፡፡ ደሟን ያወጣልኝ ነው፡፡ ሌላ ምንም የምለው የለኝም” ብለዋል፡፡ ሞዴል ቀነኒ አዱኛ ዛሬ አጭር የሕይወቷ ታሪኳ በአስከሬን ሽኝት ስነስርዓት ወቅት እንደተነበበው፤ ከአባቷ አቶ አዱኛ ዋቆ እና እናቷ አስቴር መኮንን መጋት 07 ቀን 1991 ዓ.ም. በምዕራብ ሀራርጌ ዞን ዳሩ ለቡ ወረዳ ሚጫታ ከተማ መወለዷ ተነግሯል፡፡ በትምህርቷ ብርቱ ነበረች የተባለችው ቀነኒ ከአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ በውኃ መህንድስና ከተመረቀች በኋላ በኦሮሚያ ውኃ ቢሮ ለተወሰነ ጊዜ ብትሰራም ትኩረቷን ወደ ሞዴሊንግ በማድረግ እውቅናን ስለማትረፏም ተወስቷል፡፡ ቀነኒ በማስታወቂያ ሥራዎችም ዕውቅናን በማትረፍ በፊልም ሥራ ተሳትፎ እንደነበራት በሕይወት ታሪኳ ተነግሯል፡፡

ከ2015 ዓ.ም. ጀምሮ ከአርቲሰርት አንዱኣለም ጎሳ ጋር የፍቅር ግንኙነት የመሰረተችው ቀነኒ ላለፉት ሁለት ዓመታት ከአርቲስቱ ጋር አብሮ ሲኖሩ እንደነበርና ለትናንት አጥቢያ ማክሰኞ ጠዋት 10 ሰዓት ለጊዜው እየተጣራ በሚገኝ ምክንያቱ ከመኖሪያቸው 5ኛ ፎቅ ወድቃ ሕይወቷ በ25 ዓመቷ ማለፉም በታሪኳ ተነቧል፡፡

የሞዴል ቀነኒ አዱኛ ስርዓተ ቀብር ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሲፈጸምምስል፦ Seyoum Getu/DW

ስለሞዴሏ ኅልፈትና መንስኤ እስካሁን በውል የታወቀ ነገር የለም፡፡ የአዲስ አበባ ፖሊስ በይፋዊ ማኅበራዊ ገጹ እንዳስታወቀው ግን በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 3 ልዩ ቦታው ሰንሻይን ቤቶች ፊት ለፊት ከሚገኘው ውዳሴ ህንፃ ላይ ሟች ወ/ሮ ቀነኒ አዱኛ ዋቆ መጋቢት 01 ቀን 2017 ዓ/ም ከሌሊቱ 10፡00 ሠዓት አካባቢ ከ5ኛ ፎቅ ላይ ለጊዜው ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ወድቃ ለህክምና እርዳታ ወደ ያኔት ሆስፒታል እየተወሰደች ባለበት ወቅት ህይወቷ ማለፉን፤ አስከሬኗ ወደ ዳግማዊ ምኒሊክ ሆስፒታል ለተጨማሪ ምርመራ መወሰዱንና ከበረዳ ላይ በወደቀችበት ሰዓት ፖሊስ በቤቱ ውስጥ የነበረውን ባለቤቷን ድምፃዊ አንዷለም ጎሳን በቁጥጥር ስር በማዋልም ምርመራ እያጣራ መሆኑን አሳውቋል፡፡ ፖሊስ የምርምራ ስራው ሒደት ላይ በመሆኑ አሉታዊ ተፅህኖ የሚያሳርፉ ያልተረጋገጡ መረጃዎች እንዳይሰራጩም አሳስቧል፡፡

ዛሬ በቅድስት ስላሴ በተፈጸመው ስርዓተ ቀብሯ ላይ ፍቅረኛዋ አርቲስት አንዱኣለም ጎሳ በፖሊሶች በመታጀብ ተገኝቶ እርሙን በማውጣት ስርዓተ ቀብሯ ላይ ተገኝቷል፡፡

ሥዩም ጌቱ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

እሸቴ በቀለ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW