የሠላም እጦትና የሠላም ሚንስቴር
ሰኞ፣ ግንቦት 2 2013ማስታወቂያ
በልማዱ፣ በጣሙን በደራሲና መምሕር ሰይፉ መታፈሪያ አገላለፅ፣ በእንግሊዝኛ ለበሱ አማርኛ «ጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ አሕመድ ወደ ስልጣን ከመጡ----» ተብሎ ከሚጠራዉ ከመጋቢት 2010 ወዲሕ ኢትዮጵያ ሠላም የላትም።መሪዋ ግን ለሠላም ጥረታቸዉ የዓለምን ምርጥ የሰላም ሽልማት ኖቤልን ተሸልመዋል።የሠላም ሚንስቴር መስሪያ ቤትም ተመስርቶባታል።ሠላም ለምን ራቃት? መንግስቷስ ሠላም ለማስፈን ለምን ተሳነዉ?የሠላም ሚንስትር ሙፈሪያት ካሚልን ጠይቀናል።ኢትዮጵያ ባለፉት 3 ዓመታት የገጠሟትን ፈርጀ ብዙ ችግሮችና የመንግስታቸዉን እርምጃዎች በሰፊዉ አስረድተዉናል።«የ3 ዓመቱን ሒደትና ዉጤት ለመረዳት» ይላሉ ሚንስትሯ «በገለልተኛ ስሜት መቃኘት ያስፈልጋል።»
ነጋሽ መሐመድ
ኂሩት መለሰ