1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የሠራተኞች ማሕበራት በገቢ ግብር ማሻሻያ ዙሪያ ለመንግሥት ጠንካራ መከራከሪያ አቀረቡ

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 8 2017

የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማሕበራት ኮንፌደሬሽን ፕሬዝዳንት ካሳሁን ፎሎ ትናንት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የገቢ ግብር ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ዙሪያ በተደረገ ውይይት ላይ እንዳሉት "ሠራተኛው በቀን አንድ ጊዜ በልቶ መዋል አልቻለም"።

Äthiopien Kassahun Follo
ምስል፦ CETU

የመንግስት ሰራተኞች በኑሮ ውድነት በእጅጉ እየተፈተኑ መሆናቸውን ኢሰማኮ ገለጸ

This browser does not support the audio element.

የሠራተኞች ማሕበራት በገቢ ግብር ማሻሻያ ዙሪያ ለመንግሥት ጠንካራ መከራከሪያ አቀረቡ

ኢትዮጵያ ውስጥ ከ14 ሺህ ብር በላይ ወርሃዊ ደሞዝ የሚያገኝ ተቀጣሪ ሠራተኛ ለግብር፣ ለተጨማሪ እሴት ታክስ እና ለጡረታ በድምሩ እስከ 57 በመቶ ገቢው እንደሚቆረጥበት ተገለፀ።

የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማሕበራት ኮንፌደሬሽን ፕሬዝዳንት ካሳሁን ፎሎ ትናንት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የገቢ ግብር ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ዙሪያ በተደረገ ውይይት ላይ እንዳሉት "ሠራተኛው በቀን አንድ ጊዜ በልቶ መዋል አልቻለም"።

ረቂቅ አዋጁ ከመጽደቁ በፊት ዳግም እንዲታይ አጥብቀው ያሳሰቡት ፕሬዚዳንቱ "የኑሮ ጫናውን ሊቋቋም አልቻለም" ካሉት የሠራተኛው ክፍል መካከል "አንዳንዶች ከሥራ ወጥተው ሆቴል አካባቢ ፌስታል ይዘው ይለምናሉ" ሲሉ በምሬት ተናግረዋል።

የደሞዝ ጭማሪው «ሳይመጣ የሄደ ተስፋ» ወይስ ደጓሚ ?

ኮንፌደሬሽኑ በኢትዮጵያ ዝቅተኛ የሠራተኞች የደሞዝ ወለል ወይም፤ ግብር መከፈል ያለበት ወርሃዊ ክፍያቸው ከ8,324 ብር በላይ ከሆኑት ላይ ሊሆን ይገባል ቢልም መንግሥት ባቀረበው ረቁቅ ማሻሻያ ላይ ግን ከ2000 ብር ጀምሮ የሚል አማራጭ አቅርቧል።

የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማሕበራት ኮንፌደሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ካሣሁን ፎሎ ትናንት በገቢ ግብር ረቂቅ ማሻሻያ ዙሪያ በተደረገ ውይይት ላይ እንዳሉት ከ14 ሺህ ብር በላይ ወርሃዊ ደሞዝ የሚያገኝ ሠራተኛ ኑሮውን እየመራ ያለው ከገቢው ተቀናንሶ በሚተርፈው 43 በመቶ የተጣራ ገንዘብ ብቻ ነው።

"14 ሺህ ብር በላይ የሚያገኝ ሰው 35 በመቶ ይከፍላል [ግብር]። 15 በመቶ በሚበላው ምግብ፣ በሚገዛው ዕቃ ላይ የተጨማሪ ዕሴት ግብር- ታክስ ይከፍላል። ለጡረታ 7 በመቶ ይቆረጥበታል። [በድምሩ] 57 በመቶ አሁን ከደሞዙ ላይ ይቆረጣል"።

በሠራተኞች ላይ ሥጋት ፈጥሮ የነበረው የአደጋ ሥጋት ሕግ ማሻሻያ ተደረገበት

ኢሰማኮ ከ8,300 ብር በታች ወርሃዊ ደሞዝ የሚከፈላቸው ሠራተኞች ግብር ሊከፍሉ አይገባም በሚል ለመንግሥት ጥያቄ ካቀረበ ሰንብቷል። የገንዘብ ሚኒስቴር ግን 1,200፣ 1,600፣ ወይስ 2,000 ብር ከሚከፈላቸው በላይ ይሁን የሚሉ ሦስት አማራጮችን ያቀረበ ቢሆንም 2000 የሚለው ሚዛን የደፋ ይመስላል። ይህ ካሁኑ እርምት እንዲደረግበት ነው አቶ ካሳሁን ትናንት ብርቱ ጥሪ ያደረጉት።

"ቁጥር ሳይሆን የሰውን ሕይወት እዩ። የሰውን ኑሮ እዩ" ።

ሠራተኛው ለሀገር ዕድገት፣ ለጋራ ልማት፣ ለልዩ ልዩ ተግባራት መዋጮዎችን በማድረግ ድጋፍ ሲያደርግ የነበረ ነው ያሉት አቶ ካሳሁን፣ በዚህ ወቅት "የኑሮ ጫናውን ሊቋቋም አልቻለም" ሲሉ "አንዳንድ" ያሏቸው ሠራተኞች ጉርስ ልመና ላይ መሆናቸውም ይታወቅ ሲሉ ተደምጠዋል።

«እኛ ላይ የደረሰው ነገር የሚመጣው የጤና ባለሙያ ትውልድ ላይ ቀንበሩ እንዲያርፍ አንፈልግም» ወጣት ሀኪም

"ቋሚ ኮሚቴው [የፕላን በጀት እና ፋይናንስ] ፈቃደኛ ከሆነ ከሥራ ሲወጡ ቆመን አብረን ማየት እንችላለን አንዳንድ ሠራተኞች ፌስታል ይዘው ሆቴል አካባቢ ይለምናሉ ከሥራ ወጥተው"።

በዚሁ ምክር ቤት ውስጥ ሠራተኞች ምሳ ሠዓታቸውን የእምነት ተቋማት በመሆድ እንደሚያሳልፉ መገለጹ ይታወሳል። የምክር ቤቱ አባላትም የማትጊያ እና የጥቅማጥቅም ማሻሻያ እንዲደረግላቸው የአባላት ሥነ ምግባር ደንብ ላይ ሰሞኑን ሲወያዩ ጠይቀዋል። በዚሁ የትናንቱ ውይይት ላይ ከተሳተፉ ሰዎች መካከል አንደኛዋም ይህንኑ አስረግጠው አንስተዋል።

ኮንፌደሬሽኑ በኢትዮጵያ ዝቅተኛ የሠራተኞች የደሞዝ ወለል ወይም፤ ግብር መከፈል ያለበት ወርሃዊ ክፍያቸው ከ8,324 ብር በላይ ከሆኑት ላይ ሊሆን ይገባል ቢልም መንግሥት ባቀረበው ረቁቅ ማሻሻያ ላይ ግን ከ2000 ብር ጀምሮ የሚል አማራጭ አቅርቧል።ምስል፦ Solomon Muchie/DW

"መኖር እያቃተን ነው። ሠራተኛው መኖር እያቃተው ባለበት ኹኔታ ሌላ ተጨማሪ ጫና መጫኑ ፍትሐዊ አይደለም"።

አንድ ለ አንድ ፦ ከኢትዮጵያ የሠራተኛ ማኅበራት ኮንፈደሬሽን ፕሬዝዳንት ጋር

በምንዛሪ አስተዳደር ለውጡ ምክንያት በሁሉም መስክ ዋጋ መጨመሩን ያስታወሱት የኢሰማኮ ፕሬዝዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ "ሠራተኛው በቀን አንድ ጊዜ በልቶ መኖር የለበትም ወይ?" ሲሉም ጠይቀዋል።

"በቀን አንድ ጊዜ በልቶ መዋል አልቻለም [ሠራተኛው]።

ትናንት የ2018ን የተሟላ የሁሉም ዘርፎች እና ሀገራዊ የልማት እቅድን ለመገምገም የሚኒስትሮች ምክር ቤት መሰብሰቡን ያስታወቁት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ "በ2017 የሥራ ዘመን ትርጉም ያለው" ያሉት እና "ለመጪው የ2018 የቀጠለ የዕድገት ጉዞ ጠንካራ መሠረት የሚሆን ዕድገት ፈፅመናል" ሲሉ ጽፈዋል።


ሰለሞን ሙጬ
ታምራት ዲንሳ
ማንተጋፍቶት ስለሺ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW