የሠራተኞች አድማ በኮይሻ ኃይል ማመንጫ
ዓርብ፣ ሚያዝያ 11 2011ማስታወቂያ
ከአካባቢው የሚውጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በአሁኑ ወቅት በሥራ ማቆም አድማው ምክንያት የኃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታ ሥራ ሙሉ በሙሉ እንደተቋረጠ ይገኛል። ከአካባቢው የሚውጡ መረጃዎች እንዳሚያመለከቱት በሥራ ማቆም አድማው ምክንያት የኃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታው አሁንም ሙሉ በሙሉ እንደተቋረጠ ይገኛል። በአሁኑ ውቅትም የፕሮጀክቱ አመራሮች ከሠራተኞቹ ጋር ድርድር በማካሄድ ላይ እንደሚገኙም ለማወቅ ተችሏል።
ዘግይቶ በደረሰን ዜና ደግሞ ሠራተኞቹ ዛሬ ሲያደረጉት የነበረውን ድርድር አሁን ማምሻወን በማጠናቀቅ ከነገ ቅዳሜ ጀምሮ ወደሥስራ ገበታቸው ለመመለስ ከስምምነት ላይ ደርሰዋል። ሠራተኞቹ ከስምምነት ላይ ሊደርሱ የቻሉት የአስተዳደር በደል ፈድመዋል በሚል ቅሬታ ሲነሳባቸው ከነበሩት የፕሮጅክቱ የሥራ ሃላፊዎች መካከል ሁለቱ ከሥራቸው በመታገዳቸው መሆኑም ተሰምቷል። የዲ ደብሊው ታማኝ ምንጮች እንዳረጋገጡት እገዳ የተጣለባቸው ሁለቱ ሃላፊዎች የግድቡን ግንባታ በኮንትራት እያከናወነ በሚገኘውና ሳሊኒ በተባለው ኩባንያ ወስጥ በከፍተኛ የሰው ሀብትና የፋይናንስ ኃላፊነት ቦታዎች በማገልገል የነበሩ መሆናችው ታውቋል።
ሸዋንግዛው ወጋየሁ
ሸዋዬ ለገሠ
ማንተጋፍቶት ስለሺ