የሠዎች ለሰዎች ዕቅድ
ሐሙስ፣ ጥር 7 2007ማስታወቂያ
ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚንቀሳቀሰዉ የጀርመን ግብረ-ሠናይ ድርጅት ሰዎች ለሰዎች በተጀመረዉ የጎርጎሮሳዉያን 2015 ዓመት በተለያዩ የኢትዮጵያ ገጠራማ አካባቢዎች አስራ-አንድ ፕሮጀክቶችን እንደሚሠራ አስታወቀ።በጀርመን የሰዎች ለሰዎች ቦርድ አባልና በኢትዮጵያ የድርጅቱ ሐላፊ ፔተር ራይነር ለጋዜጠኞች እንደነገሩት ድርጅታቸዉ ለዕቅዱ ማስፈፀሚያ ከ420 ሚሊዮን ብር በላይ መድቧል።አንጋፋዉ ግብረ-ሠናይ ድርጅት በሙስና ሠበብ ነባር ለጋሾቹ ሸሽተዉታል የሚለዉን ዘገባም ሐላፊዉ አስተባብለዋል።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ነጋሽ መሐመድ
ተክሌ የኋላ