1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢጋድ ሚኒስትሮች ስብሰባ

ረቡዕ፣ የካቲት 22 2015

በአባል ሀገራት መካከል የስራ ቅጥር እና የሰራተኞች ነጻ እንቅስቃሴ ላይ የተነጋገረውየ 2015 የ የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለሥልጣን (ኢጋድ)ስብሰባ የአባል ሀገራት ሰራተኛ ዜጎች በቀጠናው ያለምንም ችግር በነጻነት ተንቀሳቅሰው የሚሰሩበትን መንገድ እንደዚሁም ሕጋዊ የስራ ፈቃድ የሚያገኙበት ሕግ እና አሰራር ላይ ተወያይቷል።

Äthiopien | IGAD Treffen
ምስል Hanna Demissie/DW

የስራ ቅጥርና የሰራተኞች ነጻ እንቅስቃሴ በኢጋድ አባል ሀገራት

This browser does not support the audio element.

የምስራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግስታት ባለሥልጣን(ኢጋድ) አባል ሀገራት ሁለተኛው የሚኒስትሮች ስብሰባ ከሰኞ ጀምሮ አዲስ አበባ ውስጥ እየተካሄደ ነው። የአባል ሀገራት የስራና ቅጥር ሚኒስትሮች እና የዘርፉ አዋቂዎች እንዲሁም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለሞያዎች የሚሳተፉበት የዚህ ስብሰባ ትኩረት የስራ ቅጥር ፣ የሰራተኞች ነጻ እንቅስቃሴና የሰራተኞች ፍልሰት ነው።የ 2015 የ የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) በዓባል ሀገራት መካከል የስራ ቅጥር እና የሰራተኞች ነጻ እንቃቃሴ በተመለከተ ቀዳሚ አጀንዳ አድርጎ የጀመረው ሁለተኛው የ ኢጋድ  ስብሰባ አባል ሀገራት ሰራተኛ ዜጎቻቸው በቀጠናው ያለምንም ችግር በነጻነት ተንቀሳቅሰው ስራ የሚሰሩበትን መንገድ  እንደዚሁም ህጋዊ የስራ ፈቃድ የሚያገኙበትን ሕግ እና አሰራር ላይ እየተወያየ ነው ።የመፍትሄ ሀሳባም ያመነጫል ተግባራዊ የሚሆንበትን መንገድ ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል። እስካሁን በተሰሩት እና በቀረቡት ፖሊሲዎች ላይ ግምገማና ውይይትም ያካሂዳል። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር  በ 2021 በጅቡቲ በቀረበው የስምምነት ሰነድ(የጂቡቲ ዲክላሪሽን) መሰረት አባል ሀገራቱ ዜጎቻቸው ያለምንም ተፅእኖ  ሰብዓዊ መብታቸው በተጠበቀ መልኩ በሕጋዊ መንገድ የስራ ዝውውር ፣ ቅጥር በሀገራቱ መካከል በሚያደርጉበትን ቅድመ ሁኔታ ላይም ለመነጋገር የተቀመጠው ስብሰባ የደረሰበትን የመፍትሄ ሀሳብ ለሚንስትሮች ስብሰባ ያቀርባል ። 
ኢትዮጵያ በዚህ ስብሰባ ላይ በዋናነት እየተሳተፈች ነው ያሉት ዶ/ር ተካልኝ አያሌው የስራና ክህሎት ሚኒስቴር የአሰሪና ሰራተኞች ዘርፍ የስራ አሰፈፃሚ  ኢትዮጵያ
የምስራቅ አፍሪካ ቀጠና የፍልሰት አስተዳደር በሚል የተመሰረተውን ህብረት ጨምራ በምስራቅ አፍሪካ ቀጠና ውስጥ የተለያዪ ማህበራትን በሀላፊነት እና በአባልነት እንደምትመራ ለ DW ተናግረዋል  ።በኢትዮጵያ በሚንስትር ደረጃ አዲስ የተቋቋመው የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ይህንንኑ ለማሳለጥ ታስቦ የተቋቋመ ነው ያሉት ዶ/ር ተካልኝ  ስልጠናን የስራ እድል ፈጠራን  የሰራተኛ መብትን ሁሉንም በአንድ ለይ አሳልጠን  እየሰራን በመሆኑ ለሌሎች የምስራቅ አፍሪካ አባል ሀገራት ሞዴል ሆነናል ይላሉ ።በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አስገዳጅ ምክንያቶች ኢትዮጵያን እና ኤርትራን ጨምሮ  ዓባል ሀገራቱ  ከአፍሪቃ ህዝቦቻቸው በብዛት ከሚፈልሱባቸው ሀገራት ewseጥ ይገኙበታል።ከዚህ በተጨማሪ ኢትዮጵያ የተላያዩ  ሀገራት ስደተኞች መዳረሻም ጭምር ናት ይህንንስ በተመለከተ የታሰበ ነገር እንዳለ DW የጠየቃቸው በዓለም አቀፉ የሰራ ድርጅት ከፍተኛ አማካሪ አቶ ኤፍሬም ጌትነት መልስ ሰጥተዋል። ዝርዝሩን ሙሉውን ዘገባ ስታዳምጡ ታገኙታላችሁ። ሱዳን ፣ደቡብ ሱዳን ፣ጅቡቲ ኢትዮጲያ ፣ ሱማሊያ ፣ ኬንያ ፣ኡጋንዳ እና ኤርትራን በዓባልነት የያዘው የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ስብሰባ በያዝነው ሳምንት መጨረሻ ይጠናቀቃል   
ሀና ደምሴ 

ኂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW