1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሥራ አጥ ቁጥር በኢትዮጵያ

ዓርብ፣ ኅዳር 30 2015

እንደጎርጎሮሳዊው ጊዜ አቆጣጠር፣ በ2050 በሃገሪቱ ለሥራ ብቁ የሚሆነው ዜጋ ቁጥር ወደ 188 ሚሊዮን እንደሚያድግ ትንበያዎች ያሳያሉ። በየዓመቱ ባለው ከፍተኛ የሥራአጥ ቁጥር ላይ፣ ሌሎች ሁለት ሚሊዮን አዳዲስ ስራ ፈላጊዎች የሥራ ገበያውን እየተቀላቀሉ መሆኑን አቶ ንጉሡ ይናገራሉ።

Nigusu Tilahun
ምስል Tariku Hailu/DW

በኢትዮጵያ በየዓመቱ 2 ሚሊዮን ተጨማሪ ሥራ አጥ ይመዘገባል

This browser does not support the audio element.

 

ኢትዮጵያ ዉስጥ የስራ ፈላጊዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እጨመረ መምጣቱን  የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አስታወቀ። የሐገሪቱ የሥራ ክሒሎት ሚንስትር ደ ኤታ ንጉሡ ጥላሁን እንደሚሉት በየዓመቱ 2 ሚሊዮን ሥራ ፈላጊዎች የሥራአጡን ቁጥር ይቀየጣሉ።አቶ ንጉሱ እንደሚሉት የሥራ አጡ ቁጥር ከገጠር በከተማ፣ ከወንዱ የሴቱ ከፍ ያለ ነዉ።መንግስታቸዉ በበኩሉ በየዓመቱ 3 ሚሊዮን አዳዲስ የሥራ ዕድሎች ለመፍጠር አቅዷል።


መንግስት፣የሥራ አጥነት ችግርን በአጥጋቢነት ለመቀነስ፣በየዓመቱ ሦስት ሚሊዮን ያህል አዳዲስ የሥራ ዕድሎች የመፍጠር ዕቅድ ይዞ በመንቀሳቀስ ላይ መሆኑንም አቶ ንጉሡ ጠቁመዋል።

ሚኒስትር ዴኤታውን ያነጋገራቸው የአትላንታው ወኪላችን ታሪኩ ኃይሉ ዘገባ አለው።

በሥራና ክህሎት ሚኒስትር የሥራ፣የሥራ ስምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ንጉሡ ጥላሁን፣በኢትዮጵያ ያለውን የሥራ አጥ ዜጎች ምጣኔ በተለያየ ደረጃ ከፋፍለው አስቀምጠውታል።

እንደጎርጎሮሳዊው ጊዜ አቆጣጠር፣በ2050 በሃገሪቱ ለሥራ ብቁ የሚሆነው ዜጋ ቁጥር ወደ 188 ሚሊዮን እንደሚያድግ ትንበያዎች ያሳያሉ።በየዓመቱ ባለው ከፍተኛ የሥራ አጥ ቁጥር ላይ፣ ሌሎች ሁለት ሚሊዮን አዳዲስ ስራ ፈላጊዎች የሥራ ገበያውን እየተቀላቀሉ መሆኑን አቶ ንጉሡ ይናገራሉ።

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከመቋቋሙ በፊት የ10 ዓመት የሃገሪቱ የሥራ ዕድል ፈጠራ የድርጊት መርሐግብር ተነድፏል የሚሉት ሚኒስትር ዴኤታው፣በዚህም በ2017 ዓ ም ለ14 ሚሊዮን፣በ2022 ዓ ም ደግሞ ለ20 ሚሊዮን ዜጎች፣ የሥራ ዕድል እንዲፈጠር መንግስት ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል ተብሎ መታቀዱን አስረድተዋል።

በዚህም መሰረት፣ በኢትዮጵያ በየዓመቱ የሥራ አጥነትን በአጥጋቢ ሁኔታ ለመቀነስ በየዓመቱ ሦስት ሚሊዮን ያህል አዳዲስ የሥራ ዕድሎች የመፍጠር ዕቅድ ይዞ በመስራት ላይ መሆኑን አቶ ንጉሡ ገልጸዋል።

በ212 እና በ2013 ዓ ም፣የተቀመጠውን ዕቅድ ከሞላ ጎደል ለማሳካት የተደረገው ጥረት የተሳካ እንደነበርና፣በ214 ዓ ም ሃገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች በገጠማት ችግሮች ከታቀደው ዝቅ ብሎ መታየቱን ሚኒስትር ዴኤታው አመልክተዋል።ስለሆነም በ2015 ዓ ም ያንን በሚያካክስ ደረጃ ለመስራት ታቅዶ እንቅስቃሴ እደተካሄደ ነው ብለዋል።

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር፣የዓለም ኢንተርፕሪነርሺፕ ሳምንትን በማሰብ፣"ሚሊዮን ፈተናዎች፤ለሚሊዮን ዕድሎች"በሚል መሪ ቃል፣በሃገር አቀፍ ደረጃ በተለያዩ ኹነቶች አክብሯል።

ሚኒስትር ዴኤታው እንዳሉት፣የዚህ በዓል ዓላማም ኢንተርፕሪነርሺፕ ተገቢውን ትኩረት አግኝቶ፣ዜጎች ችግር ፈቺ አስተሳሰብ፣ባህሪና ስነ ምግባር ተላብሰው ሥራ ጠባቂ ሳይሆኑ፣ችግሮችን ወደ ወርቃማ ዕድል በመቀየር ሥራና ሀብት ፈጣሪ እንዲሆኑ ለማበረታታት ነው።

በመሆኑም፣በተለይ በውጭ ያሉ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ባለሃብቶች፣ጀማሪ የንግድ ዐሳቦችን በመደገፍ፣የሥራ አጡን ዜጋ ቁጥር ለመቀነስ የሚደረገውን ጥረት እንዲያግዙ አቶ ንጉሡ ጥሪ አቅርበዋል።

ታሪኩ ኃይሉ 

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW