1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሩሲያዉ የቅጥረኛ ወታደሮች ኩባንያ ባለቤት ፕሪጎዥን ሞተዋል?

ሐሙስ፣ ነሐሴ 18 2015

የሩሲያ የዓየር በረራ ደሕንነት ባለስልጣናት እንዳስታወቁት አንዲት የግል ጄት ከሞስኮ ወደ ሳይንት ፒተርስበርግ በመብረር ላይ እያለች ወድቃ በመከስከሷ አሳፍራቸዉ የነበሩ 10 መንገደኞችና ሰራተኞች በሙሉ ሞተዋል

የሩሲያዉ የቅጥረኛ ወታደሮች ኩባንያ ባለቤት የቭጌኒይ ፕሪጎዥን
የሩሲያዉ የቅጥረኛ ወታደሮች ኩባንያ ባለቤት የቭጌኒይ ፕሪጎዥንምስል Razgruzka_Vagnera/telegram/AP/picture alliance

ፕሪጞዢን ተጠራጣሪ፣ጠንቃቃ፣አሳሳችም በመሆናቸዉ መሞታቸዉን ማረጋገጥ አስቸግሯል

This browser does not support the audio element.

ቫግነር የተባለዉ የሩሲያ የቅጥረኛ ወታደሮች ኩባንያ ባለቤት የቭጌኒይ ፕሪጎዥኒ ትናንት በደረሰ የአዉሮፕላን አደጋ መሞታቸዉ በሰፊዉ እየተዘገበ ነዉ።የሩሲያ የዓየር በረራ ደሕንነት ባለስልጣናት እንዳስታወቁት አንዲት የግል ጄት ከሞስኮ ወደ ሳይንት ፒተርስበርግ በመብረር ላይ እያለች ወድቃ በመከስከሷ አሳፍራቸዉ የነበሩ 10 መንገደኞችና ሰራተኞች በሙሉ ሞተዋል።

የቫግነር ኩባንያ ዋና መስሪያ ቤት-ሳይንት ፒተርስበርግ ለፕሪጎዥን መታሰቢያ የተዘጋጀምስል Str/AFP/Getty Images

ከተሳፋሪዎቹ ዝርዝር ዉስጥ የየቭጌኒይ ፕሪጎዢን ስም አለበት።ይሁንና ፕሪጎዢን የተለያዩ አደጋዎችን በዘዴ የሚያልፉ፣ተጠራጣሪና ጠንቃቃ በመሆናቸዉ መሞታቸዉን እስካሁን በግልፅ ማረጋገጥ አልተቻለም።የዩናይትድ ስቴትሱን ፕሬዝደንት ጨምሮ የምዕራብ ሐገራት ፖለቲከኞች ግን የሩሲያዉ ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ፕሪጎዢን ሳያስገድሉ አይቀርም እያሉ ነዉ።

ይልማ ኃይለሚካኤል

ነጋሽ መሐመድ

ማንተጋፍቶት ስለሺ
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW