የሩስያ የዩክሬን ወረራና የኔቶና የአውሮጳ ኅብረት ምላሽ
ሐሙስ፣ የካቲት 17 2014ማስታወቂያ
ሩስያ ዛሬ የዩክሬንን ድንበር ጥሳ በመግባት በተለያየ አቅጣጫ ሙሉ ጥቃት ሰንዝራለች። በዩክሬን ዋና ከተማ ኪቭና በሌሎች ከተሞችም የሚሳይል ጥቃቶች እንደተፈጸማባት ዩክሬን አስታውቃለች። በጥቃቱ ወታደራዊ እዞች፣ የኪቭ ቦሪስፒል አየር ማረፊያና በተለያዩ ከተሞች የሚገኙ ህንጻዎች ዒላማ ሆነዋልም ባላለች ዩክሬን ።ወራራውን በምድርና በባህር ያካሄደችው ሩስያ በበኩልዋ የዩክሬን ጦር መሳሪያውን እንዲያስቀምጥ ጠይቃለች። ከሩስያ ጋር ተፋጦ የቆየው የሰሜን አትላንቲክ የጋራ መከላከያ ቃል ኪዳን ድርጅት በምህጻሩ ኔቶ «ሆን ተብሎ፣ለረዥም ጊዜ የታቀደና ግልጽ» ያለውን የሩስያ ወረራው አውግዟል። የመከላከያ እቅዶቹን ስራ ላይ መዋል መጀመሩን የተናገረው ኔቶ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ተጨማሪ ኃይሎችን ለማሰማራት ለጦር አዛዦቹ ተጨማሪ ስልጣን መስጠቱንም አስታውቋል። ሩስያ በበኩሏ በዩክሬን የጀመረችው ዘመቻ ግቦች ወታደራዊ ክምችትን ማስወገድ እና ሀገሪቱን ከአፍቃሪ ናዚዎች ነጻ ማድረግ ነው ብላለች። በጉዳዩ ላይ ከብራሰልሱን ወኪላችን ጋር የተደረገውን ቃለ መጠይቅ ለማዳመጥ ከታች የሚገኘውን የድምፅ ማዕቀፍ ይጫኑ።
ገበያው ንጉሴ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ