1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሩስያ ዩክሬን ጦርነት አንደኛ ዓመት

ዓርብ፣ የካቲት 17 2015

የሩስያ ዩክሬን ጦርነት ዛሬ አንደኛ ዓመት ዛሬ ሲታሰብውሏ።በተለያዩ የአውሮጳ ከተሞች የሚገኙ ህንጻዎች በዩክሬን ባንዲራ ቀለሞች አሸብርቀው ውለዋል። ትናንት የተካሄደው የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ሩስያ በዩክሬን የምታካሂደውን ውጊያ እንድታቆም እና ሠራዊቷንም ከዩክሬን እንድታስወጣ የሚጠይቅ የውሳኔ ሀሳብ አጽድቋል።

Ein Jahr Krieg in der Ukraine - Bachmut
ምስል Libkos/AP/dpa/picture alliance

ቻይና የሰላም ስምምነት ሃሳብን አቅርባለች

This browser does not support the audio element.

የሩስያ ዩክሬን ጦርነት ዛሬ አንደኛ ዓመት ዛሬ ሲታሰብውሏ።በተለያዩ የአውሮጳ ከተሞች የሚገኙ ህንጻዎች በዩክሬን ባንዲራ ቀለሞች አሸብርቀው ውለዋል። ትናንት የተካሄደው የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ሩስያ በዩክሬን የምታካሂደውን ውጊያ እንድታቆም እና ሠራዊቷንም ከዩክሬን እንድታስወጣ የሚጠይቅ የውሳኔ ሀሳብ አጽድቋል። ሩስያ ግን የውሳኔ ሀሳቡን ፋይዳቢስ ስትል አጣጥላዋለች።ጦርነቱ የተጀመረበት እለት በመታሰብ ላይ ባለበት በዛሬው ቀን ሩስያ በተለያዩ የዩክሬን ከተሞች ላይ ጥቃት መሰነዘሯ ተሰምቷል። ትናንትም በዩክሬን ባካሄደችው ድብደባ ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውንና መቁሰላቸውን አስታውቃ ነበር። ስለ ሩስያ ዩክሬን ጦርነት አንደኛ ዓመት መታሰቢያና የሩስያና የምዕራባውያን ፍጥጫ ስላስከተለው  ስጋት የብራሰልሱን ዘጋቢያችንን በስልክ አነጋግረነዋል።

ገበያው ንጉሴ

አዜብ ታደሰ 

ኂሩት መለሰ 

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW