1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሩስያ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ

ሰኞ፣ መጋቢት 10 2010

የሩስያ ፕሬዚደንት ቭላዲሚር ፑቲን ትናንት የተካሄደው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ አሸናፊ ሆኑ። ፕሬዚደንት ፑቲን እንደተጠበቀው በምርጫው  የተፎካከሯቸውን ሰባት እጩዎች በሰፊ የድምፅ ልዩነት ነው ያሸነፉት። ፑቲን በምርጫው 76,6% የመራጭ ድምፅ አግኝተዋል።

Moskau Wahlkampfbüro Putin Ansprache
ምስል Getty Images/AFP/Y. Kadobnov

ቭላዲሚር ፑቲን

This browser does not support the audio element.

ትናንት በተካሄደዉ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ያሸነፉት ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን የጦር መሳሪያ ፉክክር የማካሄድ ሀሳብ እንደሌላቸዉ ተናግረዋል። ዛሬ ባስተላለፉት መልዕክትም ከሌሎች ሃገራት ጋር ያላቸዉን ልዩነትም ለመፍታት እንደሚሰሩም ገልጸዋል። የምርጫዉ ዉጤት ከተሰማ በኋላ የቻይናዉ አቻቸዉ ሺ ዢንፒንግ የእንኳን ደስ ያልዎት መልዕክት ሲልኩ፤ የፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ማኑዌል ማክሮ በበኩላቸዉ ሩሲያን በፖለቲካ፣ ኤኮኖሚ፣ ዴሞክራሲ እና ማኅበራዊ ረገድ ለማዘመን እንዲሳካላቸዉ ተመኝተዉላቸዋል። የአዉሮጳ የፀጥታ እና የጋራ ትብብር ድርጅት በበኩሉ ምንም እንኳን ሕጋዊ የምርጫ ሂደት መኖሩን ቢታዘብም እዉነተኛ ፉክክር እና እዉነተኛ አማራጭ አልነበረም ሲል ተችቷል። መረጃዎች እንደሚጠቁሙት የሩሲያን ምርጫ ከ1,300 የሚሆኑ ዓለም አቀፍ የምርጫ ታዛቢዎች ተገኝተዉ ተከታትለዋል።

ገበያው ንጉሤ

አርያም ተክሌ

ሂሩት መለሰ

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW