የሩዋንዳው የስለላ ኃላፊ በብሪታንያ
ማክሰኞ፣ ነሐሴ 5 2007ማስታወቂያ
የርዋንዳ ብሔራዊ የስለላ እና ፀጥታ ዋና ኃላፊ የ54 ዓመቱ ኢማኑኤል ካሬንዚ ካራኬ ባለፈው ሰኔ ወር ለሥራ ጉዳይ ወደ እንግሊዝ አቅንተው ለንደን አየር ማረፊያ ላይ በፖሊስ በቁጥጥር ስር ውለው ነበር። የእንግሊዝ ፖሊስ ኃላፊውን በቁጥጥር ስር ያዋለው በስጳኝ ፍርድ ቤት ጥያቄ ነበር። ኢማኑኤል ካሬንዚ በዋስ ከተፈቱ በኋላ ከለንደን ሳይወጡ ምርመራ እየተደረገባቸው ከቆየ በኋላ ትናንት የእንግሊዝ ፍርድ ቤት ለስጳኝ አሳልፎ እንደማይሰጣቸው ውሳኔ አስተላልፏል። ኢማኑኤል ካሬንዚን የእንግሊዝ ፖሊስ በቁጥጥር ስር ያዋላቸው ለምን ነበር? ስቱዲዮ ከመግባቴ በፊት ለለንደኑ ወኪላችን ድልነሳው ጌታነህ ያቀረብኩለት የመጀመሪያ ጥያቄ ነበር።
ድልነሳው ጌታነህ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
አርያም ተክሌ