1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የርሃብ ችግርን የደቀነው ድርቅ በኦሮሚያ

ዓርብ፣ ነሐሴ 7 2013

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን አምስት ወረዳዎች ባጋጠመው የበልግ ዝናብ መጥፋትና የመኸር ዝናብ መዘግየት ከ420 ሺህ በላይ ዜጎች ርዳታ ለመጠበቅ መገደዳቸውን የዞኑ አደጋ ስጋት መምሪያ ገለጸ።

Äthiopien | Wahlen | Oromia

«ምዕራብ አርሲ ዞን 5 ወረዳዎች ድርቅ ማንዣበቡ»

This browser does not support the audio element.

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን አምስት ወረዳዎች ባጋጠመው የበልግ ዝናብ መጥፋትና የመኸር ዝናብ መዘግየት ከ420 ሺህ በላይ ዜጎች ርዳታ ለመጠበቅ መገደዳቸውን የዞኑ አደጋ ስጋት መምሪያ ገለጸ። በዞኑ የሻላ ወረዳ ነዋሪ ለዶይቼ ቬለ እንደተናገሩት የመጠጥ ውሃ ጭምር ከሌሎች ስፍራዎች እየመጣ በውድ ገዝተው እንደሚጠቀሙና አሁን ላይ ለከፋ ርሃብና ችግር መዳረጋቸውን ነው የገለጹት። የክልሉ መንግሥት ቅድመ ማስጠንቀቂያና አደጋ ስጋት ቅነሳ በበኩሉ በዝናብ እጥረት እና የአንበጣ መንጋ ወረራ ምክንያት የርሃብ ስጋት የተደቀነባቸው በክልሉ 10 ዞን ውስን ወረዳዎች ከፌዴራል መንግሥትና ከርዳታ ሰጪ ተቋማት ጋር በመሆን ምላሽ ለመስጠት ጥረት እያደረኩ ነው ይላል።

ስዩም ጌቱ

ሸዋዬ ለገሠ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW