የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ሕይወት እና የቤተክርስትያኒቱ መጻዒ ጊዜ
ዓርብ፣ ሚያዝያ 17 2017
የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ርዕሠ-ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ባለፈው ሰኞ ነበር ነበር ከዚህ ዓለም ድካም የማረፋቸው ዜና የተሰማው ። የቫቲካኑን የቅዱስ ፔጥሮስ መንበር በመረከብ ከደቡባዊ የአሜሪካ ክፍለ ዓለም የመጡ የመጀመሪያው አቡንም ነበሩ ።
ከረዥም የህመም ጊዜ በኋላ ያረፉት ፍራንሲስ 88 ዓመታቸው ነበር። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በመንበረ ጴጥሮስ ለማገልገል ከተመረጡበት ዕለት ጀምሮ የነበረውን አገልግሎታቸውን እንዲሁም ከርሳቸው ማለፍ በኋላ ስለሚጠበቁ ጉዳዮች አንድ እንግዳ ከወደ ሀገር ቤት ጋብዘን አነጋግረናል።
አባ ጴጥሮስ በርጋ ይባላሉ በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሃዋሪያዊ ጽ/ቤት ኃላፊ ናቸው ። የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱን ዜና እረፍት የሰሙበትን አጋጣሚ ጨምሮ ከዶቼ ቬለ ጋር በነበራቸው ቃለምልልስ በርካታ ነገሮች አንስተዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በዓለም መሪዎች ሲታወሱ
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ መንበረ ጴጥሮስን ከተረከቡበት ዕለት አንስተው ያከናወኗቸውን መንፈሳዊ አገልግሎቶች ዳስሰዋል። ከህመማቸው እስከ ህልፈታቸው የነበሩ ጉዳዮችን ጨምሮ በአገልግሎት ዘመናቸው ያከናወኗቸው የሰብአዊ እና የአካባቢ ጥበቃ ተግባራትን በዝርዝር ገልጸ,ዋል። ቀጣዩ መንበr ጴጥሮስን የሚረከቡ አባት ስለሚጠብቃቸው መንፈሳዊ እና አስተዳደሪ ጉዳዮችም እንዲሁ ተዳሰዋል።
ታምራት ዲንሳ
ነጋሽ መሐመድ