የር/ሊቃነ ጳጳሳቱ ከዋሽንግተን አዲስ አበባ መግባት
ረቡዕ፣ ሐምሌ 25 2010ማስታወቂያ
ከፍተኛው መንፈሣዊ መሪ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ ጋር በአንድነት ቦሌ ኢየር ማረፊያ በደረሱበት ጊዜ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ስድስተኛ ፓትሪያርክ አቡነ ማቲያስ እና ከፍተኛ የቤተክርስትያኒቱ አባላት እና ህብረትሰኑ ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል። ከሳቸው ጋር 19 ሊቃነ ጳጳሳት፣ ካህናት እና የቤተ ክርስቲያኒቱ አገልጋዮች አብረዋቸው ወደ ሀገር የተመለሱ ሲሆን፣ ሁሉም በቅድስት ሥላሤ ካቴድራል በተዘጋጀው የፀሎት ስነ ስርዓት ላይ ተካፋዮች ሆነዋል።
ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር
አርያም ተክሌ
ሸዋዬ ለገሠ