የሮማ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ሊቀ-ጳጳስ ፍራንሲስ የቀብር ሥነ-ሥርዓት ተፈጸመ።
ቅዳሜ፣ ሚያዝያ 18 2017
ማስታወቂያ
የሮማ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ሊቀ-ጳጳስ ፍራንሲስ የቀብር ሥነ-ሥርዓት ተፈጸመ።
በቀብር ሥነ-ሥርዓቱ የጀርመን ፕረዚደንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይን ማየር እና የአሜሪካው ፕረዚደንት ዶናልድ ትራምፕን ጨምሮ ቢያንስ የ130 ሐገራት መሪዎችና ዓለም አቀፍ ዲፕሎማቶች እንደተሳተፉ ታውቋል። በቀብር ሥነ-ሥርዓቱ ከሐገራት መሪዎች እና ባለሥልጣናት በተጨማሪ ከተለያዩ ሀገራት የተጓዙ ከ250,000 በላይ ሰዎች ተገኝተዋል።
በቀብራቸው ሥነ-ሥርዓት ሊቀ ጳጳስ ፍራንሲስ በሃይማኖታዊ እና ሰብአዊ ጉዳዮች የፈጸሟቸውን ዋና ዋና ተግባራት ተወስቷል። በተለይም ስደተኞች እና ድሆችን በመርዳት ያበረከቱት አስተዋፅኦ «ቁጥር ስፍር የሌለው» መሆኑን ተገልጿል።
በሌላ ዜና በቀብሩ ሥነስርዓት የተገኙት የአሜሪካው ፕረዚደንት ዶናልድ ትራምፕ እና የዩክሬይኑ ፕረዚደንት ቮሎደሚር ዘለንስኪ ተገናኝተው መነጋገራቸውን ታውቋል። የዋይት ሃውስ የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር ስቲቨን ቼንግ «ትራምፕ እና ዘለንስኪ ዛሬ ተገናኝተው ፍሬያማ ውይይት አካሂደዋል፤ ዝርዝር ጉዳዩ ወደ ፊትይገለጻል» ማለታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር
እሸቴ በቀለ