1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሰላም ሚንስቴር ስለ ኢትዮጵያ ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ

ዓርብ፣ ኅዳር 21 2016

የሰላም ሚኒስቴር የ2016 ዓ.ም የሦስት ወራት እቅድ አፈፃፀሙን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ሲያቀርብ ጋዜጠኞች ከቋሚ ኮሚቴ አባላት የተነሱ የፀጥታ ጉዳይን የተመለከቱ በርካታ ጥያቄዎችን ብቻ ታድመው መልሶቹን ሳያደምጡ እንዲወጡ ተደረገ ። ምላሾቹ በዝግ የሚሰጡ መሆናቸውም ተገልጿል ።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሕንጻ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሕንጻ፤ አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያምስል Solomon Muche/DW

ለሰላም ሚንስትር የቀረቡ በርካታ ጥያቄዎች ምላሽ የተሰጠው በዝግ ነው

This browser does not support the audio element.

የሰላም ሚኒስቴር የ2016 ዓ.ም የሦስት ወራት እቅድ አፈፃፀሙን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ሲያቀርብ ጋዜጠኞች ከቋሚ ኮሚቴ አባላት የተነሱ የፀጥታ ጉዳይን የተመለከቱ በርካታ ጥያቄዎችን ብቻ ታድመው መልሶቹን ሳያደምጡ እንዲወጡ ተደረገ ።  ምላሾቹ በዝግ የሚሰጡ መሆናቸውም ተገልጿል ። የሰላም ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ታየ ደንደአ ከቋሚ ኮሚታው ለተነሱ ጥቂት ጥያቄዎች ግን ለመገናኛ ብዙኃን አጭር ምላሽ ሰጥተዋል።

ኢትዮጵያ ውስጥ በንፁሐን ላይ ጉዳት እየደረሰ፤ እየሞቱ፤ እየታገቱ፤ ገንዘብ እየተጠየቀባቸው፤ ስለመሆኑ እንዲሁም የሕዝብ የመንቀሳቀስ መብት ስለመገደቡ ከቋሚ ኮሚቴው ተጠቅሶ ችግሩን ለመፍታት የፌዴራል እና የክልል መንግሥታት ምን ሠሩ የሚሉ ጥያቄዎች ተነስተዋል ።  ለእነዚህን እና ሌሎች ጥያቄዎች የተሰጡ ምላሾች ምን እንደሆነ እንዳይከታተሉ ጋዜጠኞች ጥያቄዎቹን ብቻ አድምጠው እንዲወጡ ተደርገዋል ። 

የሰላም ሚኒስቴር

በአማራ ክልል አሁን የተፈጠረው ግጭት  ሊከሰት እንደሚችል ቀደም ብሎ ተለይቶ የነበረ ቢሆንም «ችግሮችን ከመፍታት፣ አፋጣኝ ምላሽ ከመስጠት አኳያ በሚመለከታቸው አካላት የፍጥነት እና የቅንጅት ችግር ስለሚታይ እዚህ ደረጃ ደርሷል» ሲሉ የሰላም ሚኒስትር ድኤታ ታዬ ደንደአ ተናገሩ ።  

ሚኒስትር ድኤታው ይህንን የተናገሩት የሰላም ሚኒስቴር የ2016 ዓ.ም የሦስት ወራት እቅድ አፈፃፀሙን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለውጭና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሲያቀርብ ከአባላቱ «አማራ ክልል የተፈጠረው ግጭት እና ለግጭቱ አመላካች የሆኑ ነገሮች ቀድሞ አልነበሩም ወይ» በሚል ለቀረበ ጥያቄ ምላሽ ሲሰጡ ነው። ሰላም ሚኒስቴር «በአንዳንድ አካባቢዎች ያሉ የፀጥታ ችግሮች ለሰላም ግንባታ እንቅፋት የሆኑበት» ሁኔታ መኖሩን ገልጿል። 

ኢትዮጵያ ካለፉት ጥቂት ዓመታት ወዲህ ከጦርነት አዙሪት ውስጥ ተዘፍቃለች ምስል Ben Curtis/AP/dpa/picture alliance

በሌላ በኩል ከቋሚ ኮሚቴው ኢትዮጵያ ውስጥ ደቡብ ኦሞ ዞን በዳሰነች ወረዳ ከኬንያ የሚነሱ ሰዎች በአካባቢው ህብረተሰብ ላይ በተሽከርካሪ ጭምር ታግዘው ጥቃት በማድረስ ፣ በተለይ በቱርካና ሐይቅ ላይ ዐሣ በማስገር የተሰማሩ ወጣቶች ላይ ግድያ እየፈፀሙ ንብረታቸውንም እየዘረፉ በመሆኑ መንግሥት ምላሽ እንዲሰጥ ተጠይቋል።

ለሰላም ሚኒስቴር ምን ምን ጥያቄዎች ቀረቡ?

የሰላም ሚኒስቴር ዛሬ ባቀረበው የሦስት ወራት የሥራ አፈፃፀም ዘገባው የጎሣ ግጭቶች ስለመቀነሳቸው ፣ በክልሎች ውስጥ እንጂ፣ በክልሎች መካከል የሚደረግ ግጭትም እየቀነሰ ስለመሆኑ አስታውቋል። ሰላም ሚኒስቴር ይህንን ቢልም ከቋሚ ኮሚቴው ግን ብዙ ጥያቄዎች ቀርበው ነበር። «ግጭቶች መታየት እና የታጠቁ ኃይሎች ሕግን የመጣስ፣ ሰላምን የማደፍረስ ምክንያት በንፁሃን ዜጎች ሕይወት፣ ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ፣ ንፁሃን እየታገቱ ገንዘብ እየተጠየቁ» ስለመሆኑ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ምላሽ እንዲሰጥ ተጠይቃል። 

ለዚህ እና ለሌሎች የቀረቡ ዋና ዋና ጥያቄዎች የሰላም ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎች የሰጡት ምላሽ ምን እንደሆን እንዳይከታተሉ ጋዜጠኞች የሰላም ሚኒስቴርን ሪፖርት እና የቋሚ ኮሚቴውን ጥያቄዎች ብቻ ታድመው እንዲወጡ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በመታዘዙ ምላሹን ለማድመጥ አልተቻለም። ይህ ለምን ይሆናል ብለን ላቀረብነው ጥያቄም «በዝግ የሚደረግ» መሆኑን ከመግለጽ በቀር ዝርዝር ማብራሪያ አልተሰጠም። 

የሰላም ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ታየ፤ ፎቶ፦ ከማኅደርምስል Shewangizaw Wegayehu/DW

የግጭት ቅድመ ማስጠንቀቂያዎች ለምን አይተገበሩም ? 

ለሰላም ሚኒስቴር አመራሮች ሌሎች ጥያቄዎችም ቀርበው ነበር። «ኢትዮጵያ ውስጥ የሚነሱ ግጭቶች በተለይ አሁን አማራ ክልል ያለው ፣ ኦሮሚያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ያለው ጉዳይ ከግጭትም አልፎ የውስጥ የትጥቅ ግጭት - ከዚያም ሲያልፍ ወደ የእርስ በርስ ወደሚመስል ነገር የሚሄዱ ነገሮች ናቸው የሚመስሉት።»  የግጭት ቅድመ መከላከልን በተመለከተ ከቋሚ ኮሚቴው አባላት ቀርቧል። ብዙኃን መገናኛዎች የሚኒስቴሩን ምላሽ እንዳይዘግቡ አቋማቸው አለመከልከሉን የገለፁት የሰላም ሚኒስትር ዳኤታ አቶ ታየ ደንደአ ከቋሚ ኮሚታው ለተነሱ ጥቂት ጥያቄዎች ለመገናኛ ብዙኃን አጭር ምላሽ ሰጥተዋል። በዚህም በአማራ ክልል ያለው ጦርነት ሊከሰት እንደሚችል ቅድመ ትንተና እንደነበር፣ ሆኖም ግን በሚመለከተው ባሉት ግን በግልጽ ባልጠቀሱት አካል አፈጣኝ ርምጃ ባላመውሰዱ እዚህ ደረጃ ላይ መድረሱን ገልፀዋል።

«ኢትዮጵያ ውስጥ የሚነሱ ግጭቶች በተለይ አሁን አማራ ክልል ያለው ፣ ኦሮሚያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ያለው ጉዳይ ከግጭትም አልፎ የውስጥ የትጥቅ ግጭት - ከዚያም ሲያልፍ ወደ የእርስ በርስ ወደሚመስል ነገር የሚሄዱ ነገሮች ናቸው የሚመስሉት።» ምስል AP/picture alliance

ከፋኖ ቃል አቀባይ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ

«ችግሮችን ከመፍታት ፣ አፋጣኝ ምላሽ ከመስጠት አኳያ በሚመለከታቸው አካላት የፍጥነት እና የቅንጅት ችግር ስለሚታይ እዚህ ደረጃ ደርሷል።» መንግሥት በትግራይ ክልል ከሕወሓት ጋር የከረመበትን አውዳሚ ጦርነት ፣ ለ አምስት ዓመታት በኦሮሚያ ክልል ከኦነግ ሸኔ ጋር የዘለቀበትን ግጭት ለመፍታት እያደረገ ያለውን ጥረት በበጎ የጠቀሱት አቶ ታዬ በአማራ ክልል ከፋኖ ጋር የገባበትም ጦርነት በዚያው መንገድ "ሊታይ ይችላል የሚል እምነት" እንዳላቸው ገልፀዋል።

ከኬንያ የሚነሱ ሰዎች ደቡብ ኦሞ ላይ ግድያና ዝርፊያ እየፈፀሙ ነው

ለሰላም ሚኒስቴር ከቋሚ ኮሚቴው ከቀረቡት ጥያቄዎች መካከል ደቡብ ኢትዮጵያ ውስጥ ባለው የደቡብ ኦሞ ዞን ኢትዮጵያ ከኬንያ ጋር በምትዋሰንበት የዳሰነች ወረዳ ዝርፊያ፣ ግድያ እየተባባሰ ነው የሚለው ይገኝበታል። ዝርፊያውንም ሆና ግድያውን የሚፈፅሙት ከኬንያ የሚነሱ እና በተሽከርካሪ ጭምር ታግዘው ጥቃት የሚያደርሱ ወሮበሎች መሆናቸው ተገልጿል። እነዚህ ከጎረቤት ሀገር ኬንያ የሚነሱ ሰዎች በቱርካና ሀይቅ ላይ ዐሣ በማስገር የተሰማሩ ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች ላይ ግድያ ከመፈፀም አልፈው ንብረታቸውንም እየዘረፉ እንደሚገኙ ተነግሯል።

ብዙኃን መገናኛዎች የሚኒስቴሩን ምላሽ እንዳይዘግቡ አቋማቸው አለመከልከሉን የገለፁት የሰላም ሚኒስትር ዳኤታ አቶ ታየ ደንደአ ከቋሚ ኮሚታው ለተነሱ ጥቂት ጥያቄዎች ለመገናኛ ብዙኃን አጭር ምላሽ ሰጥተዋል። በዚህም በአማራ ክልል ያለው ጦርነት ሊከሰት እንደሚችል ቅድመ ትንተና እንደነበር፣ ሆኖም ግን በሚመለከተው ባሉት ግን በግልጽ ባልጠቀሱት አካል አፈጣኝ ርምጃ ባላመውሰዱ እዚህ ደረጃ ላይ መድረሱን ገልፀዋል። «ችግሮችን ከመፍታት ፣ አፋጣኝ ምላሽ ከመስጠት አኳያ በሚመለከታቸው አካላት የፍጥነት እና የቅንጅት ችግር ስለሚታይ እዚህ ደረጃ ደርሷል።»

በትግራይ ጦርነት ወቅት ታንክ ሜዳው መሀል መንገዱ ላይ ይታያል ። ፎቶ፦ ከማኅደርምስል Yasuyoshi Chiba/AFP

መንግሥት እና የፋኖ ታጣቂዎች

መንግሥት በትግራይ ክልል ከሕወሓት ጋር የከረመበትን አውዳሚ ጦርነት ፣ ለአምስት ዓመታት በኦሮሚያ ክልል ከኦነግ ሸኔ ጋር የዘለቀበትን ግጭት ለመፍታት እያደረገ ያለውን ጥረት በበጎ የጠቀሱት አቶ ታዬ በአማራ ክልል ከፋኖ ጋር የገባበትም ጦርነት በዚያው መንገድ «ሊታይ ይችላል የሚል እምነት» እንዳላቸው ገልፀዋል። ከኬንያ የሚነሱ ሰዎች ደቡብ ኦሞ ላይ ግድያና ዝርፊያ እየፈፀሙ ነው ። ለሰላም ሚኒስቴር ከቋሚ ኮሚቴው ከቀረቡት ጥያቄዎች መካከል ደቡብ ኢትዮጵያ ውስጥ ባለው የደቡብ ኦሞ ዞን ኢትዮጵያ ከኬንያ ጋር በምትዋሰንበት የዳሰነች ወረዳ ዝርፊያ፣ ግድያ እየተባባሰ ነው የሚለው ይገኝበታል።

ዝርፊያውንም ሆና ግድያውን የሚፈፅሙት ከኬንያ የሚነሱ እና በተሽከርካሪ ጭምር ታግዘው ጥቃት የሚያደርሱ ወሮበሎች መሆናቸው ተገልጿል። እነዚህ ከጎረቤት ሀገር ኬንያ የሚነሱ ሰዎች በቱርካና ሀይቅ ላይ ዐሣ በማስገር የተሰማሩ ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች ላይ ግድያ ከመፈፀም አልፈው ንብረታቸውንም እየዘረፉ እንደሚገኙ ተነግሯል።

ሰለሞን ሙጬ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW