የሰላም ባንክ ምስረታ በሀዋሳ
ሐሙስ፣ ሚያዝያ 28 2013ማስታወቂያ
በኢትዮጲያ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ የሚረዱ የመፍትሄ ሀሳቦችን የሚያሰባስብ፣ የሚያከማችና ሥራ ላይ የሚያዉል «የሰላም ባንክ» የተባለ ማዕከል አዋሳ-ዉስጥ ተመሰረተ ። ባለፈዉ ማክሰኞ በይፋ የተመሠረተዉ ማዕከል የተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢን በሚያዉከዉ ግጭትና ጥቃት ሰበብ የደፈረሰዉን ሠላም ለማጥራትና ለማርጋት የሚደረጉ ጥረቶችን ያግዛል የሚል ተስፋ ተጥሎበታል።በአንድ ግለሰብ ሐሳብ አመንጪነት የተመሰረተዉ የሰላም ባንክ ዘር፣ ፆታ፣ እድሜና የትምሕርት ደረጃ ሳይለይ ሁሉንም ኢትዮጵያ በአባልነት የሚያቅፍ እንደሆነ ተነግሯል።
ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ
ነጋሽ መሐመድ
አዜብ ታደሰ