1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሰላም ንግግሩ ተስፋ እና የሀገሪቱ መጻኢ ዕጣ ፈንታ

እሑድ፣ ኅዳር 9 2016

ከወራት ዝምታ በኋላ ተፋላሚ ወገኖች ለሌላ የሰላም ንግግር በታንዛንያዋ የንግድ ከተማ ዳሬ ሰላም ተቀምጠዋል። የኢትዮጵያ መንግስት የሰላም ንግግር እየተደረገ መሆኑን ከሳምንት ዝምታ በኋላ ባለፈው ሐሙስ ነበር ይፋ ያደረገው ። የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ተደራዳሪዎቹ ከመንግስት ተወካዮች ጋር በመነጋገር ላይ መሆናቸውን ቀደም ብሎ ነበር ያስታወቀው።

Äthiopien | Feierlichkeiten zum 50. Jahrestag der Äthiopischen Oromo Liveration Front
የኦነግ ባንዲራ ምስል Seyoum Getu/DW

መንግስት ከኦሮሞ ነጻነት ጦር ጋር የሚያደርገው የሰላም ንግግር ዘላቂ ሰላም ያመጣ ይሆን ?

This browser does not support the audio element.

በኢትዮጵያ በፌዴራል መንግስቱ እና ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ኦነሰ ብሎ በሚጠራው እና መንግስት በአሸባሪነት በፈረጀው ታጣቂ ቡድን መካከል የሚደረገው ጦርነት አምስት ዓመታትን አስቆጠረ። በሀገሪቱ «ለውጥ መጣ» ከተባለበት ወቅት አንስቶ በኦሮሚያ ክልል በአብዛኖቹ አካባቢዎች የሚደረገው ጦርነት የክልሉን ህዝብ ብሎም የመላ ሀገሪቱን  ሰላም ከማናጋት አልፎ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት እንዲፈጸም ፣ ንጹኃን በጅምላ እና በተናጥል እንዲገደሉ ፣ ለዓመታት ከኖሩበት ቤት ንብረታቸው እንዲፈናቀሉ ፣ ሀብት ንብረታቸው እንዲወድም እና መውደ,ቂያ እንዲያጡ ምክንያት ሲሆን ፤ ሀገሪቱ ችግሩን በንግግር መፍታት ተስኗት ለፖለቲካዊ ቀውስ ተዳርጋ ቆይታለች።

ለኦሮሚያው ግጭት ዘላቂ እልባት ከየት ይምጣ?

ለችግሮች ፖለቲካዊ የመፍትሄ ከመፈለግ ይልቅ  የኃይል አማራጭን መከተል የሁለቱም ወገኖች ምርጫ መሆኑ ለቀውሱ መባባስ በምክንያትነት ይጠቀሳል።  በሀገሪቱ በህዝብ ብዛትም ሆነ በቆዳ ስፋት የመጀመሪያውን ደረጃ በሚይዘው የኦሮሚያ ክልል ችግሩ እየሰፋ መምጣቱን ተከትሎ  በሌሎች ክልሎች ላለው የጸጥታ መደፍረስ እና የእርስ በእርስ ግጭት መስፋፋት የራሱን ሚና መጫወቱ ሲገለጽ ቆይቷል።

ተደራዳሪዎች ሳይስማሙ ቢለያዩም ተስፋ አያስቆርጥም ፤ አስተያየት ሰጭዎች

በክልሉ የተንሰራፋው ግጭት መዲናዋ አዲስ አበባ አፍንጫ ስር ድረስ መድረሱ ፣ አሁንም ድረስ ለዜጎች በየዕለቱ መገደል፣ መታገት ፣ መታሰር አልያም መሰወር  በአጠቃላይ በሰላም ወጥቶ ለመግባት ዋስትና ለማጣቱ ምክንያት እየሆነ መምጣቱ የዜጎች የየዕለት ሮሮ ሆኗል።

በሀገሪቱ «ለውጥ መጣ» ከተባለበት ወቅት አንስቶ በኦሮሚያ ክልል በአብዛኖቹ አካባቢዎች የሚደረገው ጦርነት የክልሉን ህዝብ ብሎም የመላ ሀገሪቱን  ሰላም ከማናጋት አልፎ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት እንዲፈጸም ፣ ንጹኃን በጅምላ እና በተናጥል እንዲገደሉ ፣ ለዓመታት ከኖሩበት ቤት ንብረታቸው እንዲፈናቀሉ ፣ ሀብት ንብረታቸው እንዲወድም እና መውደ,ቂያ እንዲያጡ ምክንያት ሲሆን ፤ ሀገሪቱ ችግሩን በንግግር መፍታት ተስኗት ለፖለቲካዊ ቀውስ ተዳርጋ ቆይታለች።ምስል John Macdougall/AFP

የፌዴራሉ መንግስት በአሸባሪነት ከሰየመው የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ጋር የመጀመሪያውን የሰላም ንግግር ባለፈው ዓመት ሚያዝያ ወር ታንዛኒያ ውስጥ ቢቀመጡም ሁለቱም ወገኖ ከመግባባት መድረስ አለመቻላቸውን በሰላም ንግግሩ ማጠቃለያ ወቅት አስታውቀዋል።

መንግሥት እና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ወደ ሰላም ንግግር እንዲመለሱ ተጠየቀ

አሁን ደግሞ ከወራት ዝምታ በኋላ ተፋላሚ ወገኖች ለሌላ የሰላም ንግግር በታንዛንያዋ የንግድ ከተማ ዳሬ ሰላም ተቀምጠዋል። የኢትዮጵያ መንግስት የሰላም ንግግር እየተደረገ መሆኑን ከሳምንት ዝምታ በኋላ ባለፈው ሐሙስ ነበር ይፋ ያደረገው ።

የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ግን አዛዡ ኩምሳ ዲሪባ ወይም ጃል መሮን ጨምሮ ተደራዳሪዎች ከመንግስት ተወካዮች ጋር በመነጋገር ላይ መሆናቸውን ዘግይቶም ቢሆን ከመንግስት ቀደም ብሎ ነበር ያስታወቀው። ምስል Seyoum Getu/DW

የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ግን አዛዡ ኩምሳ ዲሪባ ወይም ጃል መሮን ጨምሮ ተደራዳሪዎች ከመንግስት ተወካዮች ጋር በመነጋገር ላይ መሆናቸውን ዘግይቶም ቢሆን ከመንግስት ቀደም ብሎ ነበር ያስታወቀው። ነገር ግን ይህ ውይይት እስከተጠናቀረበት እስከ ሐሙስ ማምሻ ድረስ ስለደረሰበት የተባለ ነገር የለም። ነገር ግን ብዙኃኑ የክልሉ ህዝብ ተፋላሚዎች ከአንዳች ስምምነት እንዲደርሱ ጽኑ ፍላጎት እና ተስፋ እንዳለው በተለያዩ አጋጣሚዎች እየገለጸ ነው።

የሳምንቱ የእንወያይ ዝግጅታችን ርዕስ  « በኢትዮጵያ መንግስት እና በኦሮሞ ነጻነት ጦር መካከል የሚደረገው የሰላም ንግግር ተስፋ እና የሀገሪቱ መጻኢ ዕጣ ፈንታ» ይሰኛል።

ታምራት ዲንሳ 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW