1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሰሜን ሱዳን ደቡባዊ ግዛት ግጭትና ርዳታ

ረቡዕ፣ ጥቅምት 21 2005

ደቡብ ሱዳን ካደችም፥ አመነች የደቡባዊ ኮርዶፋን ዉጊያ አሁንም እንደቀጠለ ነዉ።የመንግሥት ጦር አማፂያኑ ወደሚቆጣጠሩት አካባቢ ርዳታም ሆነ ሌላ ቁሳቁስ እንዳይደርስ በየስፍራዉ ኬላ አቁሞ እየተቆጣጠረ ነዉ።

Karte Sudan mit Südsudan und Darfur

የሰሜን ሱዳን መንግሥት ደቡባዊ ኮርዶፋን ግዛት ከቤት ንብረቱ የተፈናቀለዉን ሕዝብ ርዳታ ሰጪዎች እንዲረዱት ይፈቅድ ዘንድ የተባበሩት መንግሥታት፥ የአረብ ሊግና የአፍሪቃ ሕብረት ግፊት እንዲያደርጉበት ግብረ-ሠናይ ድርጅቶች ጠየቁ።የሰሜን ሱዳን መንግሥት ጦርና አማፂያን ደቡብ ኮርዶፋን ዉስጥ የገጠሙት ዉጊያ ከ160 ሺሕ በላይ ሕዝብ አፈናቅሏል።ለጋሽ ድርጅቶች እንደሚሉት ተፈናቃዩ ሕዝብ ምግብ፥ መድሐኒት መጠለያ አያገኝም።


የሰሜን ሱዳን መንግሥት ከደቡብ ኮርዶፋን አማፂያን ጋር የገጠመዉ ጦርነት የሌላ፥ ሰብአዊ ድቀት ሰበብ ከሆነ አምና ሐምሌ ዓመት ደፈነ።ጦርነቱን የሸሹ በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ ስደተኞች የኢትዮጵያ ሠፍረዋል።የዓለም ምግብ ድርጅት (WFP) እና የሌሎች እርዳታ ሰጪ ተቋማት ባለሥልጣናት እንደሚሉት ኢትዮጵያ የሰፈሩትን ስደተኞች መርዳቱ ብዙም አላሰቸገራቸዉም።

እዚያዉ ኮርዶፋን፥ የሱዳን አብዮታዊ ግንባር የተሰኘዉ አማፂ ቡድን በሚቆጣጠረዉ አካባቢ ለሠፈረዉ ተፈናቃይ እርዳታ ለማቀበል ግን የዓለም ምግብ ድርጅት ቃል አቀባይ ቻሊስ ማክዶናሕ እንደሚሉት እስካሁን ከካርቱም መንግሥት ፍቃድ አላገኙም።
            
«አማፂያኑ በሚቆጣጠሩት አካባቢ ሁኔታዉ የተወሳሰበ ነዉ።ወደ አካባቢዉ ለመግባት ገና እየተደራደርን ነዉ።WFP ሱዳን ዉስጥ ብዙ ሰዎችን ይረዳል።ዳርፉር፥ ማዕከላዊና ምሥራቃዊ ሱዳን አራት-ነጥብ-ሁለት ሚሊዮን ሕዝብ ለመርዳት እየጣርን ነዉ።የደቡባዊ ኮርዶፋን ሕዝብም ርዳታ በጣም ያስፈልገዋል።በነዚሕ አካባቢዎች በተቻለ ፍጥነት ርዳታ ማቀበል እንድንችል አበክረን እየጣርን ነዉ።»

ለወትሮዉ ምንም ወይም ትንሽ የሚታወቀዉ የሱዳን አብዮታዊ ግንባር ሐቻምና ሐምሌ ካዱግሊ ከተሰኘችዉ የደቡባዊ ኮርዶፋን ርዕሠ-ከተማ አጠገብ የሚገኙ አካባቢዎችን ከተቆጣጠረ ወዲሕ ግዛቲቱ ሠላም አታዉቅም።የሰሜን ሱዳን መንግሥት ቡድኑን ያደራጀችና የምትረዳዉ ደቡብ ሱዳን ናት በማለት ይወነጅላል።የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዝዳት ሳልቫ ኪየር ግን ዉንጀላዉን አይቀበሉትም።ይሁንና  ያሁኑ የኮርዶፋን አማፂ ቡድን አባላት የደቡብ ሱዳን ነፃ አዉጪ ጦር (SPLA/M) አካል ሆነዉ የሱዳንን መንግሥት ይወጉ እንደነበር ኪየር አልካዱም።
            
«እነዚሕ ሰዎች የSPLA/M አካል ሆነዉ አብረዉን የተዋጉ ቢሆንም ባሁኑ ዉጊያ እኛ አልተሳተፍንም።በካርቱም መንግሥትና በደቡባዊ ኮርዶፋን ሕዝብ መካካል በሚደረገዉ ዉጊያ አንሳተፍም።»

ደቡብ ሱዳን ካደችም፥ አመነች የደቡባዊ ኮርዶፋን ዉጊያ አሁንም እንደቀጠለ ነዉ።ባለፈዉ እሁድ  የካርቱም መንግሥት አየር ሐይል ጣለዉ በተባለ ቦምብ አንድ ሕፃን ሲገደል፥ ሌሎች አራት ቆስለዋል።የመንግሥት ጦር አማፂያኑ ወደሚቆጣጠሩት አካባቢ ርዳታም ሆነ ሌላ ቁሳቁስ እንዳይደርስ በየስፍራዉ ኬላ አቁሞ እየተቆጣጠረ ነዉ።

የሁለቱ ሱዳኖች ጉዳይ «ገለለልተኛ» አጥኚ የሚባሉት አጂና ኦጅዋንግ፥ የሱዳን መንግሥት በጦርነቱ ለተፈናቀለዉ ሕዝብ ርዳታ እንዳይደርስ መከልከሉ ዘር ከማጥፋት የሚቆጠር በመሆኑ መቀጣት አለበት ባይ ናቸዉ።
                       
«ወደ ደቡባዊ ኮርዶፋን የሚላክ ሰብአዊ እርዳታን ለማደናቀፍ የሚወሰድ ማናቸዉም እርምጃ በጦር ሐይል የሚያስቀጣ መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ማረጋገጥ አለበት።ይሕን በማድረግም ድርጅቱ በአካባቢዉ በረራን ማገድና፥ የካርቱም መንግሥት ሚሳዬሎች ባካባቢዉ እንዳይተኮሱ መከልከል አለበት።»

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ኦጅዋንግ ያሉትን ርምጃም ሆነ ርዳታ ሰጪዎች የጠየቁትን መፈፀም መቻል-አለመቻሉ ላሁኑ አልየለትም። 

እርዳታ ፈላጊዎችምስል Reuters

ጀምስ ሺማንዩላ

ነጋሽ መሐመድ

ሒሩት መለሰ 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW