የሰሜን ሸዋና የኦሮሚያ ዞኖች ግጭት
ሐሙስ፣ ሚያዝያ 13 2014
ማስታወቂያ
ሰሞኑን በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታና ግድም ወረዳና ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ አዋሳኝ አካባቢዎች በተደረገዉ ግጭት የተፈናቃሉ ሰዎች ዕርዳታ እንዲሰጣቸዉ እየጠየቁ ነዉ።ካለፈዉ ዕሁድ ማታ እስከ ለማክሰኞ አጥቢያ ድረስ በቀጠለዉ ግጭት በሰሜን ሸዋ ዞን ብቻ 9 ሰዎች ተገድለዋል፤ 125 ቤቶች ተቃጥለዋል፤ 3ሺህ ነዋሪዎች ተፈናቅለውም። በኦሮሚያ ዞን ደግሞ ቢያንስ የሁለት ቀበሌ ነዋሪዎች መፈናቃለቸዉ፣ ቁጥሩ ያልታወቀ ሰዉ መሞቱንም ባለሥልጣናት አስታዉቀዋል።
ዓለምነዉ መኮንን
ነጋሽ መሐመድ
እሸቴ በቀለ