የሰሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ አሁንም እየነደደ ነዉ
ሰኞ፣ ሚያዝያ 7 2011ማስታወቂያ
ከ 420 በላይ ሄክታር መሬት ላይ የደረሰው የእሳት አደጋ እስካሁን በብርቅየ እና አጥቢ እንስሳት ላይ ጉዳት ባያስከትልም በብርቅየ እና የፓርኩ መለያ በሆኑ ዛፎች፡ የወፍ ማደርያ ጎጆዎች፡ አይጥ እና ሳር ላይ ከፍተኛ ውድመት አስከትሏል በማለት የፕርኩ ችፍ ዋርደን አቶ አበባው አዛናው ለ ዶቼ ቬለ «DW» ተናግረዋል፡፡ እሳቱን በማጥፋት ሂደት ከ 7 ሽህ በላይ ህዝብ ተረባርቧል ያሉት የሰሜን ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ወርቁ ለምለሙ ችግሩ አሁን በህብረተሰቡ አቅም መፈታት የማይቻልበት ደረጃ ላይ በመድረሱ የፌዴራል መንግስት ተለየ ውሳኔ በማሳለፍ ሃብቱን እንዲታደገው ጠይቀዋል፡፡ ግጭ መንደር ላይ የሚገኘው ሙጭላ አፋፍ የተባለው ሰንሰለታማ ተራራ ላይ እየተዛመተ የነበረው እሳት ቁልቁል ከፍተኛ ውድመት እያደረሰ ሲወርድ ከርቀት የ «DW» ዘጋቢ ተመልክቷል፡፡ ይህንን የእሳት አደጋ ለመከላከል የእስራኤል የእሳት አደጋ ተከላካይ ልኡክ ስፍራወ ድረስ ገብቶ ምልከታ እያደረገ ሲሆን የኬንያ ንብረት ነች የተባለች ሰማያዊ በነጭ ቀለም የተቀባች ሄሊኮፍተር ትናንት ስፍራው ድረስ በመሄድ እሳቱን ስታጠፋ እንደዋለች እና ከጎንደር አጼ ቴዎድሮስ አውሮፕላን ማረፊያ ነዳጅ እየቀዳች ወደ ፓርኩ ስትበር ተመልክተናል፡፡
ሰለሞን ሙጬ
አዜብ ታደሰ
ማንተጋፍቶት ስለሺ