1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ፖለቲካየሩሲያ ፌዴሬሽን

የሰሜን ኮሪያና የሩሲያ ግንኙነት

ሐሙስ፣ መስከረም 3 2016

የስሜን ኮሪያው መሪ ወደ ሩሲያ ያቀኑት የጦር ጀኔራሎችን ጨምሮ ከፍተኛ ባለስልጣኖቻቸውን አስክትለው ሲሆን፤ ክፕሬዝዳንት ፑቲንና ባለስልጥኖቻቸው ጋር በመሆንም በምስራቃዊው የአገሪቱ ግዝት የሚገኘውን የጠፈር ምርምር ጣቢያ ጎብኝተዋል። መሪዎቹ በውይይታቸው የኢኦኖሚና ንግድ ትብብር አጀንዳዎችን ትኩረት ስተው እንደተወይዩ ቢገለጽም---

የሰሜን ኮሪያ መሪ ኪም ጆንግ ኡን (ከግራ) እና የሩሲያዉ ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን
የሩሲያ ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን (ከቀኝ) ለሰሜን ኮሪያዉ መሪ ለኪም ጆንግ ኡን አቀባባል ሲያደርጉላቸዉምስል Mikhail Metzel/Russian President Press Office/dpa/picture alliance

የሰሜን ኮሪያና የሩሲያ መሪዎች ስምምነት

This browser does not support the audio element.


                         
ሩሲያን የጎበኙት የሰሜን ኮሪያዉ መሪ ኪም ጆንግ ኡንና የሩሲያዉ አስተናጋጃቸዉ ቭላድሚር ፑቲን የሁለቱን ሐገራት ግንኙነት ለማጠናከር ተስማሙ።ሁለቱ መሪዎች ምስራቃዊ ሩሲያ ዉስጥ ባደረጉት ዉይይት የሁለቱን ሐገራት  የንግድና የምጣኔ ሐብት ትብብር ለማጠናከር መስማማታቸዉ በይፋ ተነግሯል።ይሁንና ታዛቢዎችና የምዕራብ መንግስታት እንደሚሉት የምዕራባዉያን መንግስታት ቀንደኛ ጠላት የሆኑት ሁለቱ ሐገራት የጦር መሳሪያ ሽያጭና ወታደራዊ ትብብርን ለማጠናከርም ሳይስማሙ አልቀረም።የኮሪያ ልሳነ ምድር የሰላም ተስፋ


የስሜን ኮሪያው መሪ ወደ ሩሲያ ያቀኑት የጦር ጀኔራሎችን ጨምሮ ከፍተኛ ባለስልጣኖቻቸውን አስክትለው ሲሆን፤ ክፕሬዝዳንት ፑቲንና   ባለስልጥኖቻቸው ጋር በመሆንም  በምስራቃዊው የአገሪቱ ግዝት የሚገኘውን የጠፈር ምርምር ጣቢያ ጎብኝተዋል። መሪዎቹ በውይይታቸው የኢኦኖሚና ንግድ ትብብር አጀንዳዎችን ትኩረት ስተው እንደተወይዩ ቢገለጽም፤ ሰሜን ኮሪያ የጦር መሳሪያዎችንና ተተኳሽ ሮኬቶችን ለሩሲያ ስለምታቀርብበትና  ሩሲያም ለወታደራዊና በተለይም ለሳቴላይት ግንባታ ግባት ሊሆኑ የሚችሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ለማቅረብ በምትችልበት አግባብ  በሰፊውና በጥልቀት ሳይወያዩ እንዳልቀሩ ነው እየተገጸ ያለው።፡
ሰሜን ኮሪያ የንውክለር የጦር መሳሪያ እንዳታበለጽግ ሩሲያ ጭምር አባል በሆነችበት የመንግስታቱ ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት የማዕቀብ ውሳኔ የተላለፈባት መሆኑ የሚትወቅ ሲሆን፤ ሩሲያ ደግሞ በተለይ ከዩክሬን ጦርነት ወዲህ በምራባውያኑ ዘንድ ክፍተኛ የማዕቀብ ውሳኔዎች  ተላልፈውባታል። ሁለቱም እራሳቸውን የምራባውያን የጥቃት ኢላማዎችና ሰለባዎች አድርገው የሚቆጥሩ ሲሆን፤ ይህ ጉብኝትና ውይይትም ክምራባውያን እየደረስባቸው ያለውን ጫናና ጥቃት ለመቋቋም በአንድነት የሚቆሙ መሆናችውን ለማሳየት ያለመ እንደሆነ ነው በብዙዎች ዘንድ የሚታመነው።  ኪም ዮንግ በተደረገላቸው ያቀባበል ስነስራትና የእራት ግብዣ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ ሩሲያ ክብሯንና አንድነቷን  ለማስጠበቅ ቅዱስና የመከላከል ጦርነት እያካሄደች ነው በማለት፤ ሩሲያ ከኢምፔሪያሊስቶች ጋር በምታካሂደው ጦርነት ስሜን ኮሪያ ከጎኗ የምትቆም መሆኑን አረጋግጣለሁ ማለታቸው በመገናኛ ብዙሀን ተዘግቧል። ፕሬዝድንት ፑቲንም የህለቱ ገሮች ወዳጅነት የቆየ መሆኑን አውስተው፤ ፕሬዝዳንት ኪም በዚህ ወቅት ግብዥቸውን ተቀብለው ወደሩሲያ መምጥታቸው ልዩ ግምት የሚሰጠው መሆኑን  መግለጻቸው  ተጠቅሷል።
ሁለቱም በምራባያኑ የታደመባቸውና ማዕቀብ የተጣለባቸው አገሮች ከመቼውም ግዜ ይበልጥ አሁን እርስ በርሳቸው የሚፈላለጉበት ግዜ ደርሰዋል ነው የሚባለው። ስሜን ኮሪያ ከሩሲያ የእህልና ማዳበሪያ አቅርቦት፤ ከሁሉም በላይ ግን ቅድሚያ ለምትሰጠው ወታደራዊ ግንባታዋ አስፈላጊ የሆኑ ቴክኖሎጄችን ማግኘት ትፈልጋለች። ሩሲያ በበኩሏ የጦር መሳሪያዎችና ተተኳሽ ሮኬቶች ከስሜን ኮሪያ ያስፈልጓታል። በደቡብ ኮሪያ የፑሳን ዩንቨርስቲ ፕሮሰፈር የሆኑት  ሮበርት ኬሊይ እንደሚሉትም  “እነዚህ ሁለት አገሮች  ከመቺውም ግዜ ይበልጥ አሁን አንዱ አንዱን የሚፈልገበት ግዜ ነው”።  የኮሪያ ባሕረ-ሰላጤ ፍጥጫ
የሁለቱ መሪዎች ግንኙነት ከፍተኛ ወዳጅነት የተንጻባረቀበትና ውይይቶቹም በመግባባት የተጠናቀቁ ከመሆናቸው ውጭ የጦር መሳሪያ ንግድም ሆነ የቴክኖሎጂ ዝውውርን በሚመለክት  የተደረሰ  ስምምነት ስለመኖሩ በይፋ አልተገለጸም ።፡ ሆኖም ግን  አሜሪካና ምራባውያን ባጠቃላይ፤ የነዚህን “ያፈነገጡ” የሚሏቸውን መሪዎች ግንኙነትና ስምምነት ሲያወግዙና ሲያስጠነቅቁ ነው የስነበቱት።ጅፓንና ደቡብ ኮሪያ፤ ሩሲያ ከስሜን ኮሪያ ጋር የምታደረገውን ግንኙነትና ስምምነት አውግዘዋል። አሜሪካ ጉብኝቱንም ሆነ ውይይቱን መገለልና ተስፋ መቁረጥ የፈጠረው ነው ስትል የገለጸችው ሲሆን፤ የስቴት ዲፕርትሜንት ቃል አቀባዩ ሚስተር ማቴው ሚለር በዚህ  ጉዳይ  የመንግስታቸውን አቁም በመግለጽ ማስጠንቀቂያ አዘለል መልክት አስተላለፈዋል። “ አቋምችን  ግልጽ ነው። ማንኝውም ከስሜን ኮሪይ ወደ ሩሲይ የሚደረግ የጦር መሳሪያ ዝውውር የመንግስታቱ ድርት የጸጣው ምክርቤት ውሳኔዎችን የሚጥስ ነው” በማለት አገራቸው ጉድዩን እንደምትከታተለውና  አስፈላጊውን የአጸፋ እርምጃ እንድምትወስድ አስታውቀዋል። ቻይና ግን የሁለቱን አገሮች መቀራረብና መስማማት የሁለትዮሽ ጉዳይ አድርጋ እንደምታየው ነው የተገለጸው። 
የሰሜንና ደቡብ ኮሪያዎች ለየብቻቸው አገር ሁነው የተመሰረቱት  ከሁለተኛ አለም ጦርነት በኋላ እ እ በ1948 አም እንድነበር  የሚታወቅ ሲሆን፤ በያነኔዋ ሶቭየት ህብረት ቁጥጥር ስር የነበረው ስሜናዊው ክፍል ሶሻላስታዊት ስሜን ኮሪያ ስትሆን፤ በአሜሪካ  ቁጥጥር የነበርው ደቡብዊ ክፍል ደግሞ ክፒታሊስት የደቡብ አኮሪያ ሪፑብሊክ ሁና ተመሰረተች። ባሁኑ ወቅት ስሜን ኮሪያ 26 ሚሊዮን ህዝብ ያላት ሲሆን ክነጠተባባቂዎቹ 7.7 ሚሊዮን ወታደር እንዳላትም ይነገራል።የኮሪያ ልሳነ ምድር ዉዝግብ

የሰሜን ኮሪያዉ መሪ ኪም ጆንግ ኡን (ከግራ) እና የሩሲያ ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ሲወያዩምስል Vladimir Smirnov, Sputnik, Kremlin Pool Photo via AP/picture alliance
የሩሲያዉ ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን (ከፊት፣ ከግራ) ለሰሜን ኮሪያዊ መሪ ለኪም ጆንግ ኡን ገለፃ ሲያደርጉላቸዉምስል Sputnik/Mikhail Metzel/Kremlin via REUTERS

ገበያው ንጉሴ 
ነጋሽ መሐመድ

ታምራት ዲንሳ
 


 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW