1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሰሞኑ አፍሪካ ሕብረት ዉሳኔዎች በሙህሩ ዓይን

ማክሰኞ፣ የካቲት 3 2012

ትናንት ማምሻውን የተጠናቀቀው 33ኛዉ የአፍሪቃ ሕብረት የመሪዎች  ጉባኤ ሰሞኑን  አዲስ አበባ ላይ በተለያዩ አህጉራዊና ዓለም ዓቀፋዊ ጉዳዮች ላይ መክሮ ውሳኔ አሳልፏል። ከነዚህም ውስጥ የአህጉሪቱን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅና ከጦር መሳሪያ ድምጽ ነፃ የሆነች አፍሪካን ለመፍጠር የውጭ ኃይሎችን ጣልቃ ገብነት ማስወገድ ተገቢ መሆኑን አመልክቷል።

Äthiopien Addis Abeba Gipfeltreffen der Staatschefs der Afrikanischen Union
ምስል picture-alliance/AA/Palestinian Prime Ministry Office

የአፍሪቃ ሀገሮችን በኤኮኖሚና በማኅበራዊ ዘርፍ ማስተሳሰር ይበጃል።

This browser does not support the audio element.


ትናንት ማምሻውን የተጠናቀቀው 33ኛዉ የአፍሪቃ ሕብረት የመሪዎች  ጉባኤ ሰሞኑን  አዲስ አበባ ላይ በተለያዩ አህጉራዊና ዓለም ዓቀፋዊ ጉዳዮች ላይ መክሮ ውሳኔ አሳልፏል። ከነዚህም ውስጥ የአህጉሪቱን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅና ከጦር መሳሪያ ድምጽ ነፃ የሆነች አፍሪካን ለመፍጠር የውጭ ኃይሎችን ጣልቃ ገብነት ማስወገድ ተገቢ መሆኑን አመልክቷል። በሌላ በኩል የአሜሪካዉ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የነደፉትን የእስራኤልና የፍልስጤም የሰላም ዕቅድም ሕብረቱ ዉድቅ አድርጓል። በነዚህና በሌሎች  ሕብረቱ ባሳለፋቸው ውሳኔዎች ላይ ዶቼ ቬለ (DW)  ያነጋገራቸዉ በመቀሌ ዩንቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህር የሆኑት ረዳት ፕሮፌሰር የማነ ዘርዓይ እንደሚሉት ግን  ከጠቅላላው ሀብት እስከ 20 በመቶ ለጦር መሳሪያ የሚያውሉ መሪዎች ባሉባት አፍሪቃ ማድረግ የውጭ ጣልቃገብነትን በማስወገድ ብቻ ከግጭት ነፃ መሆን አይቻልም። እንደ አቶ የማነ ከዚህ ይልቅ የሕብረቱ መሪዎች ለውስጥ ሰላማቸው የሚሰጡት ትኩረትና የሚያደርጉት ጥረት ደካማ መሆን የአፍሪቃ ሃገራት ወደ ግጭት እንዲገቡ አንዱ ምክንያት ነው። ከዚህ በተጨማሪ የአህጉሪቱ መሪዎች ሕገ መንግሥታዊ ባልሆነ መንገድ ሥልጣን ለመያዝና ለማስጠበቅ የሚያደርጉት  አካሄድም ሌላው ምክንያት መሆኑን አመልክተዋል።
«ሰላም ዝም ብሎ በቀላሉ በውሳኔና በስብሰባ ሊመጣ አይችልም» የሚሉት ረዳት ፕሮፌሰር የማነ ዘርዓይ ሕብረቱ ውሳኔ ከማሳለፍ ባለፈ የአፍሪቃ ሀገሮችን በኤኮኖሚና በማኅበራዊ ዘርፍ ማስተሳሰር ለዚህም በተናጠል ከሚደረግ ጥረት ይልቅ ትኩረት ሰጥቶ በጋራ መሥራት ግጭትን በአፍሪቃ ለማስወገድ መፍትሄ መሆኑን ገልጸዋል።

ሙሉ ቅንብሩን የድምፅ ማዕቀፉን ተጭነዉ ያድምጡ።

ዮኀንስ ገ/እግዚአብሄር

ፀሐይ ጫኔ

ሽዋዬ ለገሰ
 

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW