1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አንድ መቶ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ታሰሩ

ረቡዕ፣ ነሐሴ 4 2008

አቶ ለገሰ ተፈረደኝ እንዳሚሉት ባለሥልጣናቱና አባላቱ የታሠሩት አማራ፤ ኦሮሚያ እና አዲስ አበባ መስተዳድር ዉስጥ ነዉ።ከታሠሩት መካከል አዲስ አበባ የሚገኙት ብቻ ፍርድ ቤት ሲቀርቡ የተቀሩት እስካሁን ፍርድ ቤት አልቀረቡም።

ምስል DW

[No title]

This browser does not support the audio element.

የኢትዮጵያ መንግስት የፀጥታ ሐይላት ሰሞኑን አንድ መቶ ያሕል ባለሥልጣናትና አባላቱን ማሰራቸዉን ተቃዋሚዉ የሰማያዊ ፓርቲ ዛሬ አስታወቀ።የፓርቲዉ ምክትል ፕሬዝደንት አቶ ለገሰ ተፈረደኝ እንዳሚሉት ባለሥልጣናቱና አባላቱ የታሠሩት አማራ፤ ኦሮሚያ እና አዲስ አበባ መስተዳድር ዉስጥ ነዉ።ከታሠሩት መካከል አዲስ አበባ የሚገኙት ብቻ ፍርድ ቤት ሲቀርቡ የተቀሩት እስካሁን ፍርድ ቤት አልቀረቡም።አንዳዶቹም ያሉበት ሥፍራ አይታወቅም።በምክትል ፕሬዝደንቱ መግለጫ መሠረት ከእስረኞቹ ሰላሳ-አምስቱ የፓርቲዉ የአመራር ባለሥልጣናት ናቸዉ።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ነጋሽ መሐመድ

ሒሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW