1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የሰሞንኛዉ የመንግሥታቱ ድርጅት መግለጫ «ሚዛናዊ» ተባለ

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 19 2013

የተባበሩት መንግስታት ሰሞኑን ኢትዮጵያን በተመለከተ ያወጣው መግለጫ ድርጅቱ ቀደም ሲል ይዞት የነበረውን አቋም ያጠፈ እና ሚዛናዊ ነው ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ። ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ እና ፌደራል ፖሊስ በትግራይ ክልል የደረሱ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ላይ ምርመራ እያደረጉ ሲሆን አጥፊዎች ላይ ያለምንም ምሕረት ተጠያቂነት ይከተላልም ተብሏል።

Äthiopien Botschafterin Dina Mufti
ምስል፦ Solomon Muchie/DW

የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሳምንታዊ መግለጫ

This browser does not support the audio element.

የተባበሩት መንግስታት ሰሞኑን ኢትዮጵያን በተመለከተ ያወጣው መግለጫ ድርጅቱ ቀደም ሲል ይዞት የነበረውን አቋም ያጠፈ እና ሚዛናዊ ነው ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ። ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ እና ፌደራል ፖሊስ በትግራይ ክልል የደረሱ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ላይ ምርመራ እያደረጉ ሲሆን አጥፊዎች ላይ ያለምንም ምሕረት ተጠያቂነት ይከተላልም ተብሏል። ሚኒስቴሩ በሳምንታዊ መግለጫው የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ ድርድር አሁንም በአፍሪካ መድረክ እንዲቀጥልና መቃጫ እንዲያገኝ እየተሠራ መሆኑ ተገልጿል። የኢትዮ ሱዳን የድንበር ውዝግብ ላይ ምንም አዲስ ነገር የለም ያለው የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኢትዮጵያ ጉዳዩ በሰላም ይፈታ የሚለው አቋሟን እንደያዘች መሆኑም ተነግሯል።

ሰለሞን ሙጬ

አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሐመድ 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW