የሰብዓዊ መብት ይዞታ በዚምባብዌ
ሰኞ፣ ኅዳር 29 2001ማስታወቂያ
የዋጋ ግሽበቱ ባለፈው ነሀሴ አስራ አንድ ሚልዮን ከመቶ ተመዝግቦዋል። ህዝቡ ዳቦና ቅቤ የመግዛት አቅም የለውም፡ በዚህ አስቸጋሪ ሁኔታ ሰበብም ህዝቡ ወደጎረቤት ሀገሮች ተሰዶዋል። አምባገነኑ ፕሬዚደንት ሙጋቤ የሚመሩት ባለሙሉ ስልጣኑን ገዢውን ፓርቲ እና የተቃዋሚው ቡድን ስልጣን ለመጋራት የደረሱት ፖለቲካዊው ገላጋይ ሀሳብም እስካሁን በተግባር አልተተረጎመም። በሀገሪቱ የፖለቲካ ለውጥ እንዲደረግ የሚታገለውን በምህጻሩ WOZA በሚል መጠሪያ የሚታወቀው የዚምባብዌ ሴቶችና ወንዶች ተነሱ የሚሰኘው መንግስታዊ ካልሆነ ድርጅት መስራች የሆኑት ጄኒ ዊልያምስ ባለፈው ወር የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ሽልማት አግኝተዋል። ዊልያምስን የዶይቸ ቬለ ባልደረባ ኡተ ሼፈር ሰሞኑን በበርሊን አነጋግቸዋለች።