የሰንደቅ ጋዜጣ እና የስም ማጥፋት ክስ
ማክሰኞ፣ ግንቦት 13 2005ማስታወቂያ
ጋዜጠኛ ፍሬዉ አበበ እንደገለፀዉ የፖሊስ ጥያቄ ያተኮረዉ ከወራት በፊት የቀድሞዉ ጠቅላይ ሚኒስትር ባለቤት ቤተመንግስቱን ለመልቀቅ እንዳልተዘጋጁና አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትርም ከቀድሞ መኖሪያ ቤታቸዉ እየተመላለሱ ለመስራት መገደዳቸዉ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳስከተለ በሚገልፀዉ ዘገባዉ ላይ ነዉ። የዜና ምንጩን መጠየቁን ያመለከተዉ የሰንደቅ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ከቀረበለት የስም ማጥፋት ክስ ተነስቶ ከሳሹ የቀድሞዉ ጠቅላይ ሚኒስትር ባለቤት ሳይሆኑ እንዳልቀሩ ከመገመት በቀር በትክክል የከሳሹ ማንነት እንዳልተገለፀለት አስረድቷል። ጋዜጠኛ ፍሬዉ አበበን ሸዋዬ ለገሠ አነጋግራዋለች። ባለፈዉ ሳምንት ስለሆነዉ ድርጊት በማብራራት ይጀምራል።
ሸዋዬ ለገሠ
አርያም ተክሌ