1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሰኞ መስከረም፤ 7 ፤ 2011 ዓ.ም የስፖርት ዝግጅት

ሰኞ፣ መስከረም 7 2011

በ 45ኛው የ  «BMW» የበርሊን ማራቶን  ኢትዮጵያውያን አትሊቶች ሩት አጋ እና ጥሩነሽ ዲባባ 2፥18፥34 እና 2፥18፥55 በመግባት ሁለተኛ እና ሦስተኛ ሆነዋል።

45. Berlin Marathon 2018 Neuer Weltrekord Eliud Kipchoge
ምስል Reuters/F. Bensch

ስፖርት፣ መስከረም ሰባት ቀን፣ 2011 ዓም

This browser does not support the audio element.

አትሌቲክስ

በበርሊን በተደረገው የ 45 ኛ ው የ «BMW» በርሊን ማራቶን ውድድር ኬንይዊው አትሌት ኤሉድ ኪፕቾጊ 2፥01፥39 በመግባት ኣዲስ የአለም ክብረወሰን አስመዝግብዋል።ኪፕሮቶ  2:06:23 እንዲሁም ሊላው ኪንያዊ ዊልሶን ኪፕሳጎን 2:06:48 በመግባት ሁለተኛ እና ሦስተኛ በማውጣት አሽንፍዋል።

 የ 33 ዓመቱ ኪንያዊዊ አትሌት ኪቾጊ ከውድድሩ በኋላ የተሰማኝን ደስታ ለመግላፅ ቃላት ያጥረኛል የዓለምአዲስ  ከብረወሰንን በማስመዝገቤ  ታላቅ ክብር እና ደስታ ይሰማኛል ሲል ደስታውን ገልፅዋል። የወንዶች የማራቶን ውድድር የመግቢያ ሰዓት ለ 6ኛ ግዜ መሻሻሉ ነው።በተመሳሳይ የበርሊን ሴቶች ማራቶን ውድድር ኪንያዊትዋ ግላድየስ ቺሪኖ ሁለት ሰአት ከእስራ ስምንት ደቂቃ ከእስራ እንድ ሰከንድ በመግባት አሽናፊ ሁናለች። በ 45ኛው የ  «BMW» የበርሊን ማራቶን  ኢትዮጵያውያን አትሊቶች ሩት አጋ እና ጥሩነሽ ዲባባ 2፥18፥34 እና 2፥18፥55 በመግባት ሁለተኛ እና ሦስተኛ ሆነዋል።

ምስል DW/M. Hirschmann

ቺሪኖ የበበርሊን ዘንድሮ የተካሄደዉን የማራቶን ዉድድር ጨምሮ በ 2015 እንዲሁም ያለፈው ዓመት 2017 በማሸናፍ ለ 3ኛ ግዚ የበርሊን ማራቶን ክብር አግኛታለች።

እግር ኩዋስ

በዓለም አቀፍ የወዳጅነት ጨዋታ ምክንያት እረፍት የሰነበተው ሀገራት ክለቦች የእግር ኩዋስ ጨዋታ በያዝነው ሳምንት መጨረሻ ተጀምሮዋል።  በእንግሊዝ ፕርምየር ሊግ በ አምስተኛው የጨዋታ ቀን ቅዳሜ እለት በዊንብሊ ስታድየም ሊቨርፑልን ያሰተናገዱት ቶትንሀሞች በየርገን ክሎፕ ቡድን 2 ለ 1 ተረተዋል። ቦርማውዝ ቀበሮዋችን 4 ለ 2 በመርታት ወደመጡ በት መልሶዋቸዋል።

ቸልሲ ካርዲፍን 4ለ 1 አሽንፎዋል። ጎሎቹም በፍፁም ቅጣትምት የተገኝውን ጨምሮ ኤድን ሀዛርድ 3 ጎሎችን ሲያገባ፤ ዊልያን አራተኛውን ጎል አስመዝግብዋል።

ሀደርስ ፊልድ በሜዳው በ ክርስታል ፓላስ  1ለ 0 ተረትዋል።

ምስል Getty Images/Bongarts/S. Widmann

ፍርልሀምን ያስተናገደው ማንችስተር ሲቲ ሳኒ፥ሲልቫ፥እና እስተርሊን ባስቆጠሩት  ጎሎች 3ለ 0 ፉልሃምን ረትዋል። ወደ ኒው ኣስትል ያቀናው አርሰናል ኒው ካስልን 2ለ 1 ረትዋል

ማንችስትር ዩናይትድ ቡድናቸውን ይዘው ወደዋትፈርድ የተጉዋዙት አሰልጣኝ ጆሲ ሞሪኖ አንድ ተጫዋቻቸውን በቀይ ከሚዳ አጥተው 3 ለ 1 አሸንፈው ሦስት ነጥብ ይዘው ተመልሰዋል ፥ ዎልቭስ በርሊን ሁለት ለዚሮ ኤቨርተን በ ዊስት ሀም ሦስት ለአንድ ተረትዋል ዛሪ ሳውዝ ሀምፕተን ክቭብራይተን ይጫወታል።

ሃና ደምሴ 

ነጋሽ መሐመድ 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW