1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የስፖርት ዝግጅት

ሰኞ፣ ጥቅምት 7 2015

የአንጋፋው የስፖርት ጋዜጠኛ የፍቅሩ ኪዳኔ የቀብር ስነስርዓት የፊታችን ሐሙስ ፓሪስ ፈረንሳይ እንደሚፈጸም ተነግሯል።በዚሁ እለትም በፓሪስ የሚገኙ የቅርብ ወዳጆቻቸውና ጓደኞቻቸው የአንጋፋውን የስፖርት ጋዜጠኛ ስራዎች የሚዘክርና ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና የሚቀርብበት ልዩ መርሃ ግብር በፓሪስ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ይካሄዳል።

Äthiopien Die Beerdigung von Fikru Kidane in Addis Abeba
ምስል Saint George club

የሰኞ ጥቅምት 7 ቀን 2015 ዓም የስፖርት ዝግጅት

This browser does not support the audio element.

  
በኢትዮጵያ የስፖርት ዘርፍ ፈር ቀዳጅ እንደሆነ የሚነገርለትና በተለያዩ ዓለም አቀፍ የስፖርት ተቋማት ውስጥ በሃላፊነትና እንዲሁም በአማካሪነት ያገለገለው የአንጋፋው የስፖርት ጋዜጠኛ የፍቅሩ ኪዳኔ የቀብር ስነስርዓት የፊታችን ሐሙስ ፓሪስ ፈረንሳይ እንደሚፈጸም ተነግሯል።በዚሁ እለትም በፓሪስ የሚገኙ የቅርብ ወዳጆቻቸውና ጓደኞቻቸው የአንጋፋውን የስፖርት ጋዜጠኛ ስራዎች የሚዘክርና ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና የሚቀርብበት ልዩ መርሃ ግብር በፓሪስ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ይካሄዳል። ለአንጋፋው ጋዜጠኛ ፍቅሩ ኪዳኔ ትናንት በአዲስ አበባ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ በተገኙበት የሽኝትና የጸሎት ስነ ስርዓት ተካሂዷል።ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ ያረፈው ፍቅሩ ኪዳኔ በተለያዩ የስፖርት ተቋማት በሰጠው አገልግሎትና በመገናኛ ብዙሀን ተሳትፎው በሙያ አጋሮቹና  በቅርብ በሚያውቁት ይወደሳል። ፍቅሩ በሚያውቋቸው ሰዎች እንዴት ይገለፃሉ? በዛሬው የስፖርት ዝግጅት ሃይማኖት ሁለት ሰዎችን አነጋግራለች። 

ምስል Saint George club

ሃይማኖት ጥሩነህ 

ኂሩት መለሰ


 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW