የሰደድ እሳት በአሜሪካ ደቡባዊ ካሊፎርኒያ
ሐሙስ፣ ጥር 1 2017
በአሜሪካ ደቡባዊ ካሊፎርኒያ የሰደድ እሳት ተነስቶ በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ እና የሰው ህይወት መጥፋቱ እየተነገረ ነው። በዚህ ግዛት ተለይም የብዙ ኢትዮጵያውያን መኖሪያ በሆነው የሎስ አንጀለስ ከተማ አቅራቢያ ቃጠሎው በርትቷል ተብሏል።
የሰደድ እሳቱ እስካሁን ወደ 3 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች የሀይል አቅርቦት መቋረጥ አጋጥሟቸዋል።112 ስኩየር ኮሎሜትር ላይ ጉዳት አድርሷል።ከ2000 በላይ ቤቶች እና መሰረተ ልማቶች በሙሉ ወድመዋል። ወደ 130,000 ሰዎች ቦታዉን ለቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ ተሰጥቷቸዋል። የሰደድ እሳት አደጋው በካሊፎርኒያ ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ከ50 ቢሊዮን በላይ በላይ ወጭ የሚያስወጣ ጉዳት አድርሷል።
የአደጋውን መንስኤ «ሳንትአና» የተባለው እና «ሰይጣኑ ነፋስ» የሚል ቅጥያ ያለው በየዓመቱ ከመስከረም እስከ ግንቦት በከፍተኛ ሁኔታ የሚነፍሰው ነፋስ ነው ተብሏል። ነፋሱ በዘንድሮው ዓመት በስዓት ከ160 ኪ/ሜ በላይ ፍጥነት ያለው ጠንካራ አውሎ ነፋስ ሆኖ በመከሰቱ ጉዳቱ ከፍተኛ ሆኗል።ችግሩ የተከሰው ከተማ አካባቢ መሆኑ ደግሞ ለጉዳቱ መጨመር አስተዋፅኦ አድርጓል።
በአካባቢውም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጆ እሳቱን ለመቆጣጠር ርብርብ በመደረግ ላይ ነው። ጆ ባይደንም አካባቢውን የአደጋ ቀጠና ብለው አውጀዋል።ያሰቡትን የጣሊያን ጉዞ በመሰረዝ ትኩረታቸውን ወደ አደጋው በማድረግም፤የሀገሪቱ ብሄራዊ ጥበቃ ጦር፣ የእሳት አደጋ መቆጣጠሪያ እና የሰብዓዊ ድጋፍ ወደ ቦታው እንዲዞር አዘዋል።
በሽዎች የሚቆጠሩ የእሳት አደጋ ሰራተኞች ሰደድ እሳቱን ለማጥፋት እየተረባረቡ መሆኑም ተነግሯል። ከሦስት ቀናት በኋላ ቀጠሮ የተያዘለት ዓመታዊ ግዙፉ የሆሊዉዱ የኦስካር የሽልማት መድረክ በርካቶች በሰደድ እሳቱ ቤታቸዉን ጥለዉ ቦታዉን መልቀቅ በመገደዳቸዉ ምክንያት የሽልማት መድረኩ፤ ወደ ጥር 18 ቀን መተላለፉም ተሰምቷል። ትናንት ረቡዕ በሆሊውድ ኮረብቶች ላይ የተቀሰቀሰው አዲስ የሰደድ እሳት አደጋ ቦታዉ ላይ የሚገኙትን ቱሪስቶችን ብሎም የቱሪስት መስዕብ ቦታዎችን ሁሉ አደጋ ላይ መጣሉ እየተዘገበ ነዉ። ሙሉ ቃለ ምልልሱን የድምፅ ማዕቀፉን ተጭነው ያድምጡ።
አበበ ፈለቀ
እሸቴ በቀለ
ፀሀይ ጫኔ