1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የሱዳንን ቀዉስ ያነሳዉ የአዉሮጳ ህብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ

ዓርብ፣ ሚያዝያ 27 2015

የአዉሮጳ ህብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በዓለማቀፍ ትብብብርና ልማት አጀንዳዎች ላይ ትኩረት ሰተው ተወያዩ። ዓለም ዛሬ በዩክሬኑ ጦርነት ምክኒያት ካጋጠመው የምግብ፣ የሀይልና ፋይናናስ ቀውስ ሊወጣ በሚችልበትና በዘላቂ ልማት ግቦች ስኬት ላይ ከመንግስታቱ ድርጅት የንግድና ልማት ዋን ጽሀፊ ወይዘሮ ሪብካ ግሪንስፓን ጋር ሚኒስትሮቹ በሰፈው መክረውል።

EU l Hoher Vertreter der Union für Außen- und Sicherheitspolitik, EU-Kommision - Josep Borrell
ምስል፦ Olivier Matthys/Pool via REUTERS

የአዉሮጳ ህብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባና ዉጤቱ

This browser does not support the audio element.

የአዉሮጳ ህብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ብራስልስ ላይ በነበራቸው ስብሰባ በተለይ በዓለማቀፍ ትብብብርና ልማት አጀንዳዎች ላይ ትኩረት ሰተው ተወይይተዋል። ዓለም ዛሬ በዩክሬኑ ጦርነት ምክኒያት ካጋጠመው  የምግብ፣ የሀይልና ፋይናናስ ቀውስ ሊወጣ በሚችልበትና በዘላቂ ልማት ግቦች ስኬት ላይ ከመንግስታቱ ድርጅት የንግድና ልማት ዋን ጽሀፊ ወይዘሮ ሪብካ ግሪንስፓን ጋር ሚኒስትሮቹ በሰፈው መክረውል። ሚኒስትሮቹ በአለማቀፍ ደረጃ የደረሰውን የምግብ ዕህል ዕጥረት ለመቋቋም በጥቁር  ባህር በኩል የእህል ምርት እንዲጓጓዝ የሚያስችል ስምምነት እንዲፈጠር በማድረግ በኩል የመንግስታቱ ድርጅት የተጫወተውን ሚና አድንቀዋል። 

የካውንስሉ የውጭ ጉዳይ ሀላፊና የስብሰባው መሪ ሚስተር ቦርየል፤ ህብረቱ ለዩክሬን እየሰጠ ያለውን ሁለንተናዊ ድጋፍ በመጥቀስ በተለይም በሚቀጥለው የሰኔ ወር በለንደን ሊካሄድ በታሰበው  የዩክሬን ዳግም ግንባታ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም፤ ክህብረቱና ከአለማቀፉ ማህብረሰብ የሚጠበቀውን አማልክተዋል።

ሚስተር ቦርየል በሱዳን የተክሰተው ጦርነት ያስክተለው ሰባዊ ቀውስ አሳሣቢ መሆኑንም አንስተዋል፤ “ እውነት ነው ዚጎቻችንን ከሱዳን አውተናል ግን በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሱዳኖች ካርቱምን እየለቀቁ ወደ  ግብጽና ደቡብ ሱዳን እየገቡ ነው\” በማለት ሰላማዊ ሰዎችን ለመርዳትና ደህንነታቸውን ለማረጋግጥ ግን የግድ የተኩስ አቁም ስምምነት መደረግ ያለበት መሆኑን አስታውቀዋል።

የአዉሮጳ ህብረትምስል፦ Monika Skolimowska/dpa/picture alliance

የአዉሮጳ ህብረትና ዓለማቀፉ ማህብረሰብ በሱዳን የርስ በርስ ጦርንት እንደተጀመረ ዋናው ትኩረታቸውና ጥረታቸው ዜጎቻቸውን ከአባቢው ማስወጣት እንጂ ግጭት ጦርነቱ እንዲቆምና ሰላም እንዲሰፍን አይደለም በማለት በርካቶች ወቀሳ የሚያቀርቡ ሲሆን፤ በትናንትናው ሰብሰባም ጦርነቱን ከማውገዝ ውጭ ጦርነቱን ለማስቆም የሚያስችል ተጨባጭ እርምጃ ለመውሰድ የተወሰነ ስለመሆኑ አልተገለጸም። ይልቁንም በተመሳሳይ ዕለት የአሜሪካ  የስለላ ድርጅት ከፍተኛ ሀላፊ የሆኑት ወይዘሮ  ዓቭሪል ህይነስ ለአሜሪካ ምክር ቤት ባቀረቡት ሪፖርት፤ የሱዳን ጦርነት ባጭር ጊዜ መቆሙ የሚያጠራጥር መሆኑን እንደገለጹ ነው የተሰማው “ በኛ ግምገማ በሱዳን እየተዋጉ ያሉት ሁለቱም ሀይሎች በየግላቸው ወታደራዊ ድል እናገኛለን ብለው  እስካሰቡ ድረስ ወደ ውይይት ለመምጣት ያላቸው ፍላጎት አነስተኛ ነው የሚሆነው” በማለት በዚህም ምክኒያት ጦርነቱ  ሊራዘምና የከፋና የሰፋ፤ የሰባዊና የደህንነት ቀውስም ሊያስክትል የሚችል መሆኑን  አስታውቀዋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ በሱዳን እየተከሄደ ያለው ጦርነት በፍጥነት ካልቆመ፤ የአካባቢውን አገሮች ሊያጥለቀልቅ የሚችል የስደተኖች  ቀውስ ሊከሰት እንደሚችልና ከ860ሺ በላይ ስደተኖችም ሊፈልሱና ለነዚህ መርጃም  ቢያንስ 445 ሚሊዮን ዶላር የሚያስፍልግ እንደሆነም የመንግስትቱ ድርጅት የስደተኖች መርጃ ማሳሰቡ ተገልጿል። 

በተጨማሪም ከትናንትናው የሚኒስትሮች ስብሰባ አንድ ቀን ቀደም ብሎ፤ ሩሲያ ዩክሬንን በፕሬዝንቷ ሚስተር ፑቲን  ላይ የድሮን ጥቃት ለማድረስ ሞክራለች  በማለት ክስ ማቅረቧ የሚታወስ ሲሆን፤ የህብሩቱ የውጭ ጉዳይ ሀላፊ ሚስተር ቦርየል ከጋዜጠኖች ጋር  በነበራቸው ቆይታ ክሱን የማይታመን በማለት አጣጥለውታል። ሁኒታው ግን የቅራኔውን መካረርና የጦርነቱ ደረጃም ሊለወጥ የሚችል መሆኑን አያመላክትም ወይ? የሚል ጥያቄ ቀርቦላቸው ሲመልሱም፤ “ እኛ ሩሲያ ይህን ክስ ምክኒያት በማድረግ ጦርነቱን የበለጠ እዳትገፋበት ነው ጥሪ የምናቀርበው” ብለዋል። ከሩሲያ በኩል በአንጻሩ፤ በዚህ ዩክሬን ሞክረችው ባሉት ጥቃት የሌሎችም እጅ እንዳለበት በመግለጽ፤ ሚስተር ቦርየል የሰጡትን አስተያየት ሁኒታውን በውል ያላገንዘበና  ያልተረዳ ነው በማለት ሩሲያ ለድርጊቱ ተመጣጣኝ  አጸፋ እንደምትሰጥ  ባለስልጣኖቿ ያስታወቁ መሆኑን መገኛ ብዙሀን ዘግበዋል።

የአዉሮጳ ህብረት ምስል፦ Kenzo Tribouillard/AFP/Getty Images

የሚኒስትሮቹ ስብሰባ በአጠቃላይ፤ በዩክሬን ጦርነትና በሌሎች አክባቢዎችም በሚከሰቱ ግጭቶችና ጦርነቶች የተፈጠሩ የምግብ፣ የሀይልና የፋይናንስ ችግሮችን ለመቋቋም በሚያስችሉ የልማትና  የትብብር ፕሮግራሞች ላይ የተወያዩ ቤሆንም፤ የችግሮቹ ምንጭ የሆኑት ጦርነቶች ሊቆሙ በሚችሉበት ሁኒታ የወሰዷቸው  እርምጃዎች ግን ግልጽ አይደሉም እየተባለ ነው። በዚህም ምክኒያት  ህብረቱ፤ ግጭት ጦርነቶች እንዳይነሱም ሆነ ከተከሰቱ በኋላ ፈጥኖ መፍትሄ በመፈለግ በኩል እየተዋጣለት አይደደለም በማለት መተቸት ይዟል።

ገበያው ንጉሴ

አዜብ ታደሰ

ዮኃንስ ገብረግዚአብሔር

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW