የሱዳን ቀውስ
እሑድ፣ ሰኔ 11 2015
ሱዳን በሁለቱ ጀነኔራሎቿ መካክል በተቀሰቀሰ ጦርነት የዋይታና ጩኸት ምድ ር ከሆነች ሁለት ወር ሆኗታል። እ እ እ ሚያዚያ አስራ አምስት ነበር የዛሬ ሁለት ወር በአገሪቱ የጦር አዛዥ ና ፕሬዝዳንት ጀነራል አብዴል ፋታህ አልቡርሀንና ምክትል ፕሬዝዳንቱና የፈ ጥኖ ደራሹ ጦር አዛዥ ጀነራል መሐመድ ሀምዳን ዳጋሎ ሀሎች መካከል በመሀል ካር ቱም ውጊያ የተጀመረው። ካርቱም የጦርነቱ መጀመሪያና ዋናዋ የጦር ሜዳ በመሆኗ ከፍተኛ ውድመት እን ደደርሰባትና ኑዋሪዎቿም ለሞትና ስደት እንደተዳረጉ ነው የሚገለጸው።
የመንግስታቱ ድርጅት መረጃዎች እንዳስታወቁት፤ ባለፉት ሁለት ወራት ብቻ ሁለት ሚሊዮን ሱዳኖች ተፈናቅለዋልየተረጂዎች ቁ ጥርም 25 ሚልዮን ደርሷል።በሺዎች የሚቆጠሩ ሞተዋል ወይም ጉዳት ድርሶባቸዋል ። 18 ከፍለ ሀገሮች እንደተ ስፋፋ የሚነገር ሲሆን፤ በተለይ ዳርፉር ግን በማንነት ላይ ያተኮሩ ጥቃቶች የሚፈጸሙበት በመሆኑ ከ ሁሉም ይበልጥ አደገኛ እንደሆነ ነው የሚነገረው።
፡ የመንግስታቱ ሱዳን ተወክይ ሚስተር ቮልከር ፔርትስ በሰጡት መግለጫ የፈጥኖ ደራሹ አባላት የተካተቱባቸው የአረብ ሚሊሺያዎች በሰላማዊ ሰዎች ላይ ማንነት ተኮር ጥቃቶ ች እየፈጸሙ መሆኑን የሚገልጹ ዘገባዎች እንደሚደርሷቸውና ሁኔታውም አስደን ጋጭና አሳስቢም መሆኑን አስታውቀዋል።
ፍትህ ለአፍርካ የተባለ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት የሱዳን ዳይሬክተር ሚ ስተር ሃፊዝ ሞሃመድም፤ በዳርፉር የማንነት ግጭት ታሪክ የነበረ ቢሆንም፤ አሁን ችግሩ የተባባሰው ግን በካርቱም መነግስት ባለመኖሩ ነው የሚሉት። “አሁን ችግሩ አሳስቢ ነው፤ ምክኒያቱም የካርቱሙ መንግስት ፈርሷል፡፤ ሚሊሺያዎቹ ይህንን ሁኔታ በመጠቀም ነው ጥቃት የሚፈጽሙት” በማለት ሁኔታው አደገኛ መሆኑን አሳስበዋል ።
በለንደን ስኩል ኦፍ ሀይጂን የሱዳን ምርምር ግሩፕ ዳይሬክተር ወዘሪት ማይ ሱን ደሀብም በበኩላቸው፤ አሁን በዳርፉር በተለይም በአልጄኒንና አካባቢ ያለው ሁኔታ በጣም አስከፊ መሆኑን ነው የሚናገሩት፤ “ በትክክል ሁኔታው አስደንጋጭና በቃላት ሊገለጽ ከሚቺለው በላይ ነው። እንደተረዳነው ከሆነ ግጭት ጥቃቱ እየሰፋና እየክፋም የሚሄድ ብቻ ሳይሆን በካባቢው ከነበረው የማንነት ተኮር ጥቃት ታሪክ ጋርም የተያያዘ ነው” በማለት በእስካሁኖቹ የምርምር ስራቸው እንደዚህ አይነት አስከፊ ሁኔታ አይተው እን ደማያውቁ ጭምር ገልጸዋል።
ጦርነቱን ለምስቆም የሚደረጉ ጥረቶች እሳክሁን ውጤት አላስገኙም። በአሜርካና ሳኡዲ አረቢያ አደራዳሪነት ተደርሰው የነበሩ የተኩስ ማቆም ስ ምምነቶች አንዳቸውም አልተክበሩም። ተጽኖ ፈጣሪ የሆኑ የአረብና ሌሎች መንግስታት ከሁለቱም ወይም ካንዱ የሱዳ ን ተፋላሚ ሀይል ጋር ግንኑነት እንዳላቸው ቢታወቅም፤ ጦርነቱን ማስቆም ቀርቶ ገቢራዊ የሚሆን የተኩስ ማቆም ስምምነት እንዲደረ ስ አለማስቻላቸው አነጋጋሪ ሁኗል። በተለይ የአውሮፓ ህብረትና አባል አገሮቹ ዛሬ ሙሉ ትኩረታቸውን በዩኪሬን ላይ ብቻ በማድረግ ሌላውን ችላ ብለዋል የሚሉ ትችቶችና አስተያቶችም እየተሰ ሙ ነው።
ከዚህ አንጻር ዲደብሌው የሱዳንን ችግር ህብረቱ ችላ አላለውም ወይ? ለሱዳን ብቻ ሳይሆን ለካባቢውና አውሮፓ ጭምር ችግር ሊያስክትል የሚችለው ን ጦርነት ለማስቆም ህብረቱ ምን እይደረገ ነው? በማለት ላቀረበው ጥይቄ፤ የህብረቱ ቃል አቀባይ ፒተር ስታኖ ሲመልሱ፤ “ የተኩስ ማቆሙን ስምምነት አለመከበር በሚመለክት ሁለቱን ወገኖች በጥብቅ አውግዘናል። ለዚህም ሁለቱም ናቸው ተጠያቂ የሚሆኑት። ህብረቱ ሁለቱም ወገኖች ጦርነቱን ባስቸኳይና በቋሚነት እንዲያቆሙ ጥሪውን በድጋሜ ያቀርባል" በማለት የጦርነቱ ሰለባ ህዝቡ እንደሆነና መዘዙም ለአካ ብቢው አገሮች ጭምር እንደሚተርፍ አስገንዝበዋል። በዚሁ ላይ ህብረቱ በተጨማ ሪ እያደረገ ያለውንና የሚያደርገውን ለተጠየቁት ሲመልሱም፤ “ ህብረቱ ለሁለ ቱም ወገኖች ከሚያስተላልፈው ጥሪ በተጨማሪ እንዲቀራረቡና ሰላም እንዲፈጥሩ ፤ የሚችለውን ሁሉ ያደርጋል" በማለት ይህም ከአለም አቀፉ ማሕበረሰብና አጋሮቻቸው ጋር በህብረት እንደሚሆን አስታውቀ ዋል።
ሰሞኑን በጅቡቲ የተካሂደው የምስራቅ ዓፍሪካ በይነ መንግስታት (ኢጋድ) የመ ሪዎች ጉባኤም በኬንያው ፕሬዝዳንት የሚመራና ኢትዮጵያ፣ ሶማሊያ፤ ጅቡቲና ደቡብ ሱድን የተካተቱበት ኮሚቴ በማቋቁም፤ በሱዳን ባስቸኳይ ሰላም እንዲፈጠር የሚያስችል ውሳኔ የተላለፈ መሆኑን ከ ጉባኤው የወጡ መግለጫዎች አስታውቀዋል። ይሁንና ጀነራል አልቡርሀን ከባላንጣቸው ጄነራል ሀምዳን ጋር እስከመቼውም ለውይይት አልቀመጥም ብለዋል እየተባለ ሲሆን፤ ይህም ለሱዳን ሰላም የሚደረገውን ጥረት ስኬታማነት ቢያንስ ሊያዘገየው እ ንደሚችል ነው የሚገመተው።
ገበይው ንጉሴ
ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር