የሱዳን አብዮት አንደኛ ዓመት
ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 9 2012
ማስታወቂያ
በሱዳን ሕዝባዊ አብዮት ከተቀጣጠለ አንድ ዓመት ሆነው። አብዮት ፈጥና ትመጣለች ሲባል ትቀር እና ቀረች ስትባል የምትመጣበት ጊዜ ይበረክታል። ብዙ ቦታ እንደታየው ይላል የበርሊኑ ዘጋቢያችን ብዙ ቦታ እንደታየው ሀገረ ገዢዎችን ሁሉ አባርራ ሹም ሽር አብዮት ታካሂዳለች፤ ውላ አድራም ልጆቿን ትበላለች። እንደሚታወቀው የአብዮት መነሻ ትንሽ ነገር በሱዳን ውስጥም እንዲሁ በዳቦ ላይ በተጨመረ ጥቂት ሳንቲም ሰበብ ነው ያለፈው ዓመት ሕዝባዊ አመፅ ከዳር እስከዳር የተቀጣጠለው። ምንም እንኳን የሱዳን አብዮት አንድ ዓመት ቢደፍንም የሀገሪቱ ችግር ግን እጅግ በርካታ መሆኑ ነው የሚነገረው።
ይልማ ኃይለሚካኤል
ሸዋዬ ለገሠ
እሸቴ በቀለ