1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሱዳን በወረራ የያዘችው የኢትዮጵያ መሬት ጉዳይ

ሰኞ፣ ኅዳር 17 2016

መንግሥት ሱዳን በሰሜን ጦርነት ወቅት በወረራ የያዘችውን የኢትዮጵያ መሬት በድርድር ለማስመለስ የሱዳንን ከጦርነት መውጣት እና ሰላም መሆን እየጠበቀ መሆኑን ማስታወቁ "ሱዳን ሰላም የሚሆነው መቼ ነው" የሚለውን ጥያቄ እርግጠኛ ሆኖ መመለስ ስለማይቻል የቀረበው ምክንያት ከመርህ አንፃር አሳማኝ አለመሆኑ ተገለፀ።

የኢትዮጵያ ሱዳን ድንበር
የኢትዮጵያ ሱዳን ድንበር ምስል Alemnew Mekonnen/DW

ሱዳን በኃይል የወሰደችው መሬት እንዴት ሊመለስ ታስቧል ?

This browser does not support the audio element.

መንግሥት ሱዳን በሰሜን ጦርነት ወቅት በወረራ የያዘችውን የኢትዮጵያ መሬት በድርድር ለማስመለስ የሱዳንን ከጦርነት መውጣት እና ሰላም መሆን እየጠበቀ መሆኑን ማስታወቁ "ሱዳን ሰላም የሚሆነው መቼ ነው"  የሚለውን ጥያቄ እርግጠኛ ሆኖ መመለስ ስለማይቻል የቀረበው ምክንያት ከመርህ አንፃር አሳማኝ አለመሆኑ ተገለፀ።የኢትዮ ሱዳን የድንበር ይገባኛል ውዝግብ እና ያገረሸው ስጋት

የኢትዮጵያ መንግሥት በውስጥ ችግር በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች ከታጣቂዎች ጋር ግልጽ ጦርነት እያደረገ በመሆኑ አሁን ባለበት ሁኔታ ሱዳን የኢትዮጵያ ገበሬዎችን በማፈናቀል በኃይል የወሰደችውን መሬት ለማስመለስ "ከውጭ ኃይል ጋር ጦርነት ማስተናገድ" እንደማትችል ያነጋገርናቸው የአለም አቀፍ ሕግ እና ዲፕሎማሲ ተንታኝ ግልፀዋል።

በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ኢኮኖሚዋ ከገባበት ችግር እንዲላቀቅ የኢትዮጵያ መንግሥት የውጭ ምንዛሪ ድጋፍ በሚያማትርበት በአሁኑ ወቅት ሱዳን በወረራ የያዘችውን መሬት በኃይል ለማስመለስ ቢሞክር የሚኖረው አለምአቀፍ ጫና ቀላል እንደማይሆን በማመን የተወሰደ የፖሊሲ ምርጫ ስለመሆኑ ባለሙያው ገልፀዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሦስት ወራት የሥራ ክንውኑን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ሲያቀርብ ፣ ሱዳን የኢትዮጵያን መሬት በወረራ ከያዘች ዓመታት ማለፉ ተገልጾ አሁን ድረስ "የሁኔታ ለውጥ እንደሌለ" ፣ ሆኖም ሀገሪቱ ከችግር ስትላቀቅ መሬቱን በድርድር የመመለስ አቅጣጫ ስለመያዙ ተነግሮ ነበር።

ሱዳን  በኃይል የወሰደችው መሬት እንዴት ሊመለስ ታስቧል ?

የኢትዮ ሱዳን የድንበር ውዝግብኢትዮጵያ እና ሱዳን የጋራ የድንበር ጉዳያቸውን በሰላም ለመፍታት የጋራ ኮሚሽን አቋቁመው ሥራ ሲሰሩ ቆይተዋል። ምንም እንኳን እስካሁን ተጨባጭ ውጤት ያመጣ ባይሆንም።

ይህም በመሆኑ በተለይም አልፋሽጋ በተባለውና ኢትዮጵያ በአማራ ክልል በኩል ከሱዳን ጋር በምትዋሰንበት አካባቢ በየጊዜው ግጭቶች ይከሰታሉ።

ሱዳን ኢትዮጵያ በሰሜን ጦርነት ወቅት የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ መግባቷን እንደ በጎ አጋጣሚ ተጠቅማ ይህንን የይገባኛል ጥያቄ የምታነሳበትን በኢትዮጵያ ግበሬዎች እጅ ሥር የነበረን መሬት በኃይል ተቆጣጥራ ይዛለች።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያለፉትን ሦስት ወራት የሥራ ክንውኑን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለውጭና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ያለፈው አርብ እለት ሲያቀርብ ጉዳዩ በቋሚ ኮሚቴው ተነስቶ ነበር።

በሚኒስቴሩ የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር አምባሳደት ፍሥሓ ሻውል " የሁኔታ ለውጥ እንደሌለ" እና ጉዳዩ በይደር መያዙን ተናግረዋል።

"ከወረሩት ጊዜ ጀምሮ እንደወረሩት ነው ያለው። ነገር ግን በመንግሥት ፣ በከፍተኛ አመራሩ የተያዘው አቅጣጫ እነሱ ያደረጉትን እኛ መድገም የለብንም የሚል ጽኑ አቋም ተይዟል። ሱዳን ራሷን በምትሆንበት ጊዜ ፣ ከችግር በምትላቀቅ ጊዜ በድርድር ልንጨርሰው እንችላለን የሚል ጠንካራ መከራከሪያ ነጥብ ስላለን በይደር ያቆየነው ነው"

ሱዳን መቼ ከእርስ በርስ ግጭት ትወጣለች ?

ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ያነጋገርናቸው የአለም አቀፍ ሕግ እና የዲፕሎማሲ ጉዳዮች ተንታኝ ሱዳን ወደ ሰላም ስትመለስ የሚለው አማራጭ ላይ ሀገሪቱ መቼ ወደዚያ ሁኔታ ትገባለች የሚለውን ማን በእርግጠኝነት ይመልሳል የሚል መከራከሪያ አንስተዋል።

"ለማን ያዋጣል ከተባለ የአለም አቀፍ ግንኙነት የሚመራበት መርህ በተጨባጭ እውነታዎች ፣ መሬት ላይ ባሉ ሁኔታዎች ላይ ተመስርቶ የሚገነባ እንጂ [አይዲያሊዝም] የሚመራው አይደለም። በማለት በሁኔታው ሱዳን መጠቀሟን ገልፀዋል።

ተንታኙ እንደሚሉት ይልቁንም ኢትዮጵያ ከውጭ ኃይል ጋር ጦርነት ውስጥ መግባት ስለማትፈልግ የተያዘ አቋም ስለመሆኑ ይገልፃሉ።

የኢትዮጵያ ሱዳን ድንበር ምስል DW/Alemenew Mekonnen

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር አምባሳደር ፍሥሓ ሻውል "ኢትዮጵያ ከድንበር ባሻገር ከሱዳን ጋር ያላት ግንኙነት እጅግ ታሪካዊና በርካታ ጉዳዮችን የሚያካትት በመሆኑ" ጉዳዩ በይደር መያዙን ሲገልፁ ፣ ተንታኙ ይህ መልካም ቢሆንም ኢትዮጵያ በዚህ ወቅት የተወረረ ድንበሯን በኃይል ለማስመለስ ጥረት ብታደርግ "የሚኖረው አለም አቀፍ ጫና ቀላል አይሆንም" በማለት የመንግሥትን የውሳኔ ዳራ መነሻ አብራርተዋል።

የኢትዮ-ሱዳን ድንበር ውዝግብና አንድምታው

የቅኝ ግዛት ድንበሮችና መዘዛቸው

አፍሪካ ውስጥ በተለይም ምስራቅ አፍሪካ አካባቢ በድንበር ይገባኛል ምክንያት የሚከሰቱ ግጭቶች በርካቶች ናቸው። የሀገራቱ የድንበር ወሰን የቅኝ ግዛት አደረጃጀት አሉታዊ አሻራ ያረፈበት ፣ ተመሳሳይ ማንነት ያላቸውን ማህበረስቦች የከፋፈለና በሁለትና ሦስት ሀገራት የለያየ ፣ ድንበሮቹ በሀገራቱ በጎ ፈቃድ እና ስምምነት ላይ ያልተመሰረተ ብሎም በምድር ላይ ያልተሰመሩ መኖራቸውና በግልጽ ስላልተካለሉ ደም አፋሳሽ ግጭቶች በየ ጊዜው ይታያሉ።

ሰለሞን ሙጬ

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW