1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሱዳን እና የደቡብ ሱዳን ውዝግብ

ቅዳሜ፣ ሚያዝያ 13 2004

የደቡብ ሱዳን ጦር ከአንድ ሣምንት በላይ በፊት ከያዘው የሱዳን ዋነኛ የሄጅሊጅ የነዳጅ ዘይት ምድር ወይም ደቡብ ሱዳናውያኑ እንደሚጠሩት ከፓንቱ ወታደሮቹን ማስወጣት መቀጠሉን በዛሬው ዕለት አስታወቀ።

ምስል picture-alliance/dpa

የደቡብ ሱዳን ጦር ከአንድ ሣምንት በላይ በፊት ከያዘው የሱዳን ዋነኛ የሄጅሊጅ የነዳጅ ዘይት ምድር ወይም ደቡብ ሱዳናውያኑ እንደሚጠሩት ከፓንቱ ወታደሮቹን ማስወጣት መቀጠሉን በዛሬው ዕለት አስታወቀ።  ይህን የገለጹት የደቡብ ሱዳን ማስታወቂያ ሚኒስትር ባርናባ-ማሪያል-ቤንጃሚን የወታደሮቹ መውጣት ሶሥት ቀናት እንደሚፈጅም አስረድተዋል። የድቡብ ሱዳን ፕሬዚደንት ሳልቫ ኪር ትናንት የደቡብ ሱዳን ጦር ከሄጅሊጅ እንዲወጣ ትዕዛዝ ያስተላለፉት ከተመድ እና ከአፍሪቃ ህብረት ጦራቸው አካባቢውን እንዲለቅ ግፊት በመጠናከሩ ብቻ ሳይሆን ከሱዳን ጋ ውዝግባቸውን በድርድር መፍታት ለሚቻልበት ዘዴ ዕድል ለመስጠት መሆኑን አስታውቀዉ ነበረ። የወታደሮቹ መውጣት የአሥር ቀኑን ወረራ እንደሚያበቃ ሲገምት የአሜሪካ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ ደግሞ የሁለቱ ተወዛጋቢ መንግሥታት መሪዎች በቁርጠኝነት ወደ ንግግሩ ጠረጴዛ እንዲመለሱ ጥሪ አድርገዋል። ይሁንና፡ ሱዳን አወዛጋቢውን ግዛት ራስዋ ነፃ ማውጣቷን ነው የገለፀችው። ካለፉት ጥቂት ወራት ወዲህ እየተካረረ የመጣው ውጥረት ሁለቱን ሀገሮች ወደለየለት ጦርነት እንዳያመራቸው አስግቶዋል።


አርያም ተክሌ

መሥፍን መኮንን

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW