የሱዳን ከአሜሪካን የሽብርተኝነት መዝገብ መውጣት
ረቡዕ፣ ጥቅምት 11 2013
ማስታወቂያ
ዩናይትድ ስቴትስ አሸባሪዎችን የሚደግፉ ሃገራት ናቸው ከምትላቸው ዝርዝር ውስጥ እንደምታስወጣት አስታውቃለች። ዋሽንግተን ኻርቱምን ከዚህ ዝርዝር ውስጥ ለማውጣት በጎርጎሪዮሳዊው 1998 በኬንያ እና ታንዛኒያ ዋና ከተሞች በሚገኙ ኤምባሲዎቿ ላይ አልቃይዳ ላደረሰው የቦምብ ጥቃት ከ300 ሚሊየን ዶላር በላይ ካሣ እንድትከፍል ጠይቃለች። የሱዳን የሽግግር መንግሥት የተጠየቀውን ከፍሎ ከአሸባሪዎች ዝርዝር ለመውጣት ዝግጁነቱን አመልክቷል። ከሱዳን ሌላ በአሁኑ ወቅት በአሜሪካ የአሸባሪዎች ዝርዝር ውስጥ ኢራን እና ሰሜን ኮርያ ይገኛሉ። ከብራስልስ ገበያው ንጉሤ ዝርዝሩን ልኮልናል።
ገበያው ንጉሤ
ሸዋዬ ለገሠ
አዜብ ታደሰ